የሲዳማ/ብ/ክ/መ/ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ግዥ፣ የቶታል ስቴሽንና ዲፈሬንሻል ጂፒኤስ ጥገና ግዥ፣ ፕሎተር ማሽን ጥገና መግዛት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ/ብ/ክ/መ/ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሎት የተገለጸውን ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ግዥ
- ሎት 2 የቶታል ስቴሽንና ዲፈሬንሻል ጂፒኤስ ጥገና ግዥ
- ሎት ፕሎተር ማሽን ጥገና ግዥ
በመሆኑም ተጫራቾች፣
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) እየከፈሉ ከመ/ቤቱ ግዥ ፋይናስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር ብቻ)በጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ጨረታው የቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ እና የፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ መቅረብ አለበት። ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 11ኛው ቀን 8:00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ በ8፡00 ሰአት ተዘግቶ በ8፡30 የሚከፈት ይሆናል፤
6, ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ሳይ ስማቸውንና ፊርማቸውን አድራሻቸውንና ስልክ ቁጥር ማስፈር አለባቸው፣
7. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046 221 7014 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ። የመ/ቤቱ አድራሻ ከሀዋሳ ገብርዔል ቤ/ክርስትያን ፊት ለፊት ነው።
የሲዳማ /ብ/ ክ/መ/ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-05-16
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 11ኛው ቀን 8:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-16 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 11ኛው ቀን 8:30 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: የሲዳማ ብ/ክ/መ/ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: May 05, 2026
- Posted at: 2026-05-06T11:47:09.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.