የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ቢሮን ለማስጠገን በታቀደው መሠረት ግዥውን ለመፈጸም እንዲቻል በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለማሠራት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ሕጋዊ ፊቃድ ካላቸው ተጫረቾች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ቢሮን ለማስጠገን በታቀደው መሠረት ግዥውን ለመፈጸም እንዲቻል በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለማሠራት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ሕጋዊ ፊቃድ ካላቸው ተጫረቾች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡
- በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተስማሩ፤
2. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
4. አቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው!
5, የጨረታ ስነዱን ከሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 30(ሰላሳ ) በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20/ሃያ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችው በ500 (አምስት መቶ ብር) ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 120,000 (አንድ መቶ ሀያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የተመስከረ)ሲፒኦ (CPO )ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
7. ጨረታ ሰነዱ በስም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፕ (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል)በመያዝ ተከታታይ ቀናት በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቢሮ ቁጥር 30 (ግዢ ኬዝ ቲም)ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታው በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 30 ይከፈታል፤ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል። የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
9. ማንኛውም ተጫራች በሲዳማ ክልል እና በሀዋሳ ከተማ አስተዳዳር ውስጥ ተመሳሳይ ሥራ በእጁ ላይ ካለና የሥራው አፈጻጸም 70% ካልደረሰ በጨረታ መወዳዳር አይችልም።ሥራው 70% እና በላይ የደረሰ ከሆነ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ማረጋጋጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
10. በጨረታ አከፋፈት ሥነ-ሥርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲክ ቼክ በሚደረግበት ግዜ በሁለቱ መካከል 5% (ከአምስት ፐርሰንት በላይ ልዩነት ካለ ተጫራቹ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።
11. ለጨረታ ያሰገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ላይ ከአስራ አምስት ፐርሠንት (15%)በላይ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይሆናል ።
12. ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር የቀረበው ዋጋ ከ20% በላይ በሆነ መጠን ያነሰ እና ከ30% በማይበልጥ መጠን ያነሰ ሲሆን እንደተስበረ የጨረታ ዋጋ ይቆጠራል። ከ30% በላይ ያነሰ ከሆነ ለእያንዳንዱ ሥራ ዝርዝር ተጨባጭ የወቅቱ ገበያ የዋጋ ትንተና (Direct Unit Cost Analysis sheet) ማቅረብ የሚችል እና ለዚህም መ/ቤቱ የጠየቀውን የውል ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ወይም መያዣ ገንዘብ መጠን ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል።
13. በጨረታ ማስታወቅያና በጨረታ ሰነድ ላይ ልዩነት ከተፈጠረ በጨረታ ሰነድ ላይ ያለው ይወስዳል።
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ 046 220 2077
የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-25
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-25 10:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Hawassa City High Court
- Bid bond: 120,000 (አንድ መቶ ሀያ ሺህ ብር)
- Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
- Published: May 05, 2026
- Posted at: 2026-05-06T11:51:41.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.