የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት የነባር ጎርፍ መውረጃ ቦይ ጠረጋ ሥራ በሐይቅ ዳር፣ ታቦር፣ አዲስ ክ/ከተማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ማህበራት መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት የነባር ጎርፍ መውረጃ በይ ጠረጋ ሥራ በሐይቅ ዳር፣ ታቦር፣ አዲስ ክ/ከተማ ከሎት 7 እስከ ሎት10 ድረስ ያሉትን አራት (4) ሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ማህበራት መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት፡-

1. በሥራ ዘርፉ መስኩ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤

2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣

4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣

5. በጨረታው እንዲሳተፍ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤

6. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ሕንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ “ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ለሃያ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ወስዶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የተመሰከረ ሲፒኦ (CPO ) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።

8. የጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 20 (ሃያ) ተከታታይ ቀናት ከፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዥ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 21ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት፤ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።

10. በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲክ ቼክ በሚደረግበት ጊዜ ከሁለት ፐርሰንት በላይ ሆነ በታች ልዩነት ካለ ተጫራቹ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።

11. ጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ላይ ከአሥራ አምስት ፐርሠንት (15%) በላይ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።

12. ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረቡ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ታች ከሃያ እስከ ሰላሳ ፐርሠንት (20% እስከ 30% በታች ከሆነ በተሰበረው ተብለው ተይዞ የሚያልፍ ይሆናል።

13. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 046 212-13-34

የሀዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ፋይናንስና/ኢኮ/ል/መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-25
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-25 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Hawassa City Administration Finance & Economic Development Bureau
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: May 05, 2026
  • Posted at: 2026-05-06T12:32:30.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders