Business and factory foreclosure

የአውሲ ርሱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጨው ማቀነባበርያ ፋብሪካ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍርድ ባለመብት ክብሮም ታረቀኝ ህንጻ ሥራ ተቋራጭ እና የፍርድ ባለዕዳ ሬድ ሲ ጨው ማቀነባበርያ እና ማምረቻ ኃላ/የተ/የግል ማህበር መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክርክር የፍርድ ባለዕዳ እንደፍርዱ ሊፈጽም ስላልቻለ በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አፍዴራ ወረዳ የሚገኝ የፍርድ ባለዕዳ ሬድ ሲ ጨው ማቀነባበርያ እና ማምረቻ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ንብረት የሆነ በ36.000ሜ.ካ ያለ ጅምር የጨው ማቀነባበርያ ፋብሪካ ባለበት ሁኔታ መነሻ ግምቱ ብር 19,581,402.38 (አስራ ዘጠኝ ሚልዮን አምስት መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ አራት መቶ ሁለት ከ38/100) የሆነ ንብረት በግልጽ ጨረታ በሐራጅ ይሸጣል።

  • ለንብረቱ መሸጥ ምክንያት የሆነውና በፍርድ የተወሰነው የገንዘብ ልክ ብር 8,146,668.558 (ስምንት ሚልዮን አንድ መቶ አርባ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ስምንት ከ558/100) ነው።
  • ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች በሚጫረቱበት ወቅት የንብረቱ ግምት 1/4ተኛ በቼክ ማስያዝ አለባቸው።
  • የጨረታው አሸናፊዎች አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በ5 ቀን ውስጥ አጠቃለው ገቢ ማድረግ አለበት አለባቸው።
  • የሀራጁ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናት አየር ላይ ይቆያል።
  • የጨረታው አሸናፊ የሆነ አካል በጨረታ ለገዛው ንብረት ዋጋውን ሣይከፍል ወይም ግዴታውን ሣይፈጽም ቀርቶ ንብረቱ በ2ኛ ጨረታ ቢሸጥ ዋጋው የቀነሰ እንደሆነ ልዩነቱንና ኪሣራውን እንዲከፍል ይገደዳል።

የአውሲ ርሱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-04
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የሀራጁ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናት አየር ላይ ይቆያል
  • Bid opening: 2026-06-04 12:00
  • Bid opening (note): ለተከታታይ 30 ቀናት አየር ላይ ይቆያል
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: የአውሲ ርሱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (May 06, 2026)
  • Posted at: 2026-05-06T14:06:51.000Z
← Back to all tenders