ፀደይ ባንክ አ.ማ. ለጃን ሜዳ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዘዉን በደብረ ብርሃን ከተማ የቦታዉ ስፋት 20000 ካ.ሜ የሆነ የኢንዱስትሪ ሼድ እና ቦታ ለፕሌይ ዉድና ኤምዲኤፍ ማምረቻ አገልግሎት የሚዉል በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አ.ማ. ለጃን ሜዳ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዘዉን በደብረ ብርሃን ከተማ የካርታ ቁጥር ደብኢፓ /03/00202014 የቦታዉ ስፋት 20000 ካ.ሜ የሆነ የኢንዱስትሪ ሽድ እና ቦታ ለፕሌይ ዉድና ኤምዲኤፍ ማምረቻ አገልግሎት የሚዉል በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም ተጫራቾች ለጫረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደምቦች በመገንዘብና ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ተጫራቾች እንዲጫረቱ ይጋብዛ።
- የቤቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር ግምቱ 116,435,020.15 (አንድ መቶ አስራ ስድስት ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ ዜሮ ሃያ ብር ከአስራ አምስት ሳንቲም የሆነ
- ተጫራቾች የቤቱን ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር ¼ (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ) በጸደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታዉ አሽናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠዉ የጨረታዉ ዉጤት በሚመለከተዉ አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠዉ ብቻ ይሆናል።
- በጨረታዉ የሚሳተፈዉ በህግ ሰዉነት ያገኘ ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደምብ፣ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ዉክልና ማቅረብ አለበት።
- የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ዉስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጨረታ ያሸነፈዉን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። አሸናፊዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
- በጨረታዉ ለተሸነፉ ተጫራጮች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊዉ ከሚገዛዉ ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ ጋር የተያያዙ ማናቸዉም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝዉዉሩ ጋር የሚገናኙ ማንኛዉንም ወጭዎች ገዢ ይሸፍናል/ ይከፍላል። ዉዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረዉና የክፍያ ጊዜዉ ላልደረሰ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር እንዲዋዋል ይደረጋል።
- ተጫራቾች ቤቱን /ድርጅቱን/ በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።
- ከፍ ሲል የተጠቀሰዉን ንብረት ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላና ፍላጎት ላለዉ ተጫራች በሚሰጠዉ ከፍተኛ ዋጋ ባንኩ እስከ 30% ( ስላላ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል።
- ጨረታዉ የሚካሄደዉ ሰኔ 2/2018 ከጠዋቱ 3.00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6.00 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክ/ከተማ ልዩ ቦታዉ ሰንጋ ተራ በባንኩ ዋና መ/ቤት 11ኛ ፎቅ ይሆናል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጫረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠተበቀ ነዉ።
ለተጨማሪ መረጃ፡- ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት በስ.ቁ +251 91 877 9825 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።
Tender details
- Deadline: 2026-06-09
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-06-09 12:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
- Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
- Bid bond: 25%
- Published: May 10, 2026
- Posted at: 2026-05-11T11:31:37.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.