በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለውሃ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የውሃ ሰብመርሴብል ፓምፕ እና ሞተር ከነሙሉ አክሰሰሪው በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለውሃ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የውሃ ሰብመርሴብል ፓምፕ እና ሞተር ከነሙሉ አክሰሰሪው በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ይፈልጋል።
ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች እንድትሳተፉ ይጋብዛል ።
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው ያላት
- በዘርፉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው /ያላት/
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተመሰከረለት ትክክለኛ ሲፒኦ ወይም በህጋዊ ደረሰኝ መሂ-1/፡- ማስያዝ አለባቸው፡፡
|
ሎት |
የጨረታው ዓይነት |
የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና |
|
1 |
የውሃ ሰብመርሴብስ ፓምፕ እና ሞተር ከነሙሉ አክሰሰሪው |
300
|
100000
|
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ድረስ ባሉት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሰውን የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ በመክፈል ከሲ/ዋዩ ወ/ገን/ጽ/ቤት ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡10 ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ዋጋ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ካለምንም ስርዝ ድልዝ በመሙላት ኦርጅናሉን ብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በፖስታው ላይ ስማቸውን፣ አድራሻቸውን እና የሚወዳደሩበትን የጨረታ ዓይነት በመፃፍ ሲያ/ዋ/ወ/ገን/ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ጨረታው አስከሚዘጋበት ድረስ ማስገባትይችላሉ።
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ በማጓጓዝ በፑሉ በሚገኙ ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋል።
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር በባንክ በተመሰከረ ትክክለኛ ሲፒኦ ወይም በህጋዊ ደረሰኝ መሂ-1 በማስያዝ ውል።
- ሎት 1 ዝርዝር መገለጫ ሰብመርሴብል ፓምፕ እና ሞተር ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ።
- መ/ቤቱ በግዥው ላይ 20% የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው።
- የጨረታ ውድድሩ በጥቅል ዋጋ ላይ የተመሰረተ ነው።
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
- በስልክ ቁጥር 0116200679 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-26
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-05-26 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡10
- Region: Amhara
- Publishing entity: Sideberna Wayu Woreda FEDB
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: May 11, 2026
- Posted at: 2026-05-12T07:34:33.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.