የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የሻይ ቡና መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ፣ ለፖሊስ አባላት ብርድ ልብስ ግዥ እና የሙዚቃ መሳሪያ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ግዥ
- ሎት 1፡- የሻይ ቡና መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ
- ሎት 2፡- ለፖሊስ አባላት ብርድ ልብስ ግዥ
- ሎት 3፡-የሙዚቃ መሳሪያ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታ
- ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚገልጽ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin no) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
- ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ለሎት 1 የሻይ ቡና መስተንግዶ ግዥ 50,000 ብር ሎት 2፡- የፖሊስ አባላት ብርድ ልብስ 50,000 ብር ሎት 3፡-የሙዚቃ መሳሪያ 50,000 ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፣ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከመምሪያው የግዥና ንብረት አስ/ር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 100 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሃሳብ ዋናና ኮፒ በማለት ተፈርሞበት በጥንቃቄ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቂያው ከተመለከተው የጊዜ ገደብ በፊት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ፣ የግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 100 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ መደረግ አለበት።
- ጨረታው ማስታወቂያ በወጣ 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- ይህ ጨረታ ለ60 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታወን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0471355629
የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-05-28
- Bid closing time: 14:30
- Bid closing (note): ጨረታው ማስታወቂያ በወጣ 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-28 15:00
- Bid opening (note): ጨረታው ማስታወቂያ በወጣ 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: Benchi Sheko Zone Finance Bureau
- Bid bond: 50,000 ብር ለእያንዳንዳቸው ሎቶች
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published: May 12, 2026
- Posted at: 2026-05-12T08:17:16.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.