በሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ሥር የሰላ ድንጋይ ጤና ጣቢያ የተለያዩ ስራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ሥር የሰላ ድንጋይ ጤና ጣቢያ የሚከተሉትን ሰራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።

  1. የጤና ጣቢያዉን የዉስጥ ግቢ የኮብል ድንጋይ ንጣፍና ዲች ስራ፣ 
  2. ለመድሃኒት ክፍል የሚሆን ካዉንተር እና ሸልፍ የአልሙኒየም ስራ፣
  3. የፈርኒቸር ዉጤቶችና የቢሮ እቃዎች እና
  4. የህትመት ዉጤቶች

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሞሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

1. በዘመኑ የዘርፉን የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።

2. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

4. የሚገዙ እቃዎችና የሚሰሩ ስራዎች ዓይነት በዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

5. ለእያንዳንዱ እቃ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ከዋና ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦርድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ መሂ ማስያዝ አለባቸው።

7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግ/ፋ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀን 2፡30 እስከ 6፡30 እና ከ7፡30 እስከ 11፡30 ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም በግ/ፋ/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ክፍል በ16ኛው ቀን ከ4፡30 እስከ 6፡00 ጨረታው ይከፈታል።

9. የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ለመክፈት አያግደውም።

10. በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ተጫራቾች በመመሪያው መሠረት ድጋፍ ይደረግላቸዋል።

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. አሸናፊው ድርጅት የሚለየዉ በእያንዳንዱ እቃ (በነጠላ ዋጋ) ነው።

13. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በአሸነፈበት ዋጋ በፍትህ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆነ መሆን አለበት።

14. የጨረታው መዝጊያ ቀን እሁድና ቅዳሜ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን 4፡00 ታሽጐ 4፡30 ይከፈታል።

አድራሻ፣ አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከደብረብርሃን 72 ኪሎ ሜትር ወደ ደሴ መስመር ከሚወስደው መንገድ ጣርማ በር /ዋሻ/ ወደ ምዕራብ 22 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 625 00 78 ወይም 09 15 55 79 01 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።

የሰላ ድንጋይ ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-25
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀን 2፡30 እስከ 6፡30 እና ከ7፡30 እስከ 11፡30
  • Bid opening: 2026-05-26 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከ4፡30 እስከ 6፡00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: North Shewa Zone Mojan Wereda woreda Sela Dengay Health Post
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ እቃ
  • Published: May 11, 2026
  • Posted at: 2026-05-12T11:58:59.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders