አባተ እና ትህትና ሪል እስቴት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የ23 ብሎክ ጂ+2 የመኖሪያ ቤት የሕንፃ ማሻሻያ የግንባታ ሥራ ለማሠራት ይፈልጋል

Description

አባተ እና ትህትና ሪል እስቴት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር

የሕንፃ ግንባታ የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን የ23 ብሎክ ጂ+2 የመኖሪያ ቤት የሕንፃ ማሻሻያ የግንባታ ሥራ ለማሠራት ስለፈለገ መሥፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መጫረት ትችላላችሁ።

  • የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ
  • የንግድ ሥራ ምዝገባ ፍቃድ
  • የታደሰ የኮንስትራክሽን የብቃት ማረጋገጫ
  • የብቃት ማረጋገጫቸው ደረጃ አምስት (5) እና ከዚያ በላይ
  • ተጨራቾች የጨረታ ውድድር ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ እና ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ በማሸግ በድምሩ አራት ሰንድ ለየብቻ በማሸግ እና የድርጅቱን ፊርማ ማህተም በማድረግ እንዲያቀርቡ።
  • የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO 20%) የጨረታውን የሞሉትን አጠቃላይ ዋጋ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ተጨራጮች ለ90ቀናት የሚያገለግል ወይም የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒዮ) በባንክ ትእዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (un conditional Bank Guarantee) ለዚሁ በተዘጋጀው ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች ለጨረታው ያስገባው የፋይናንሻል ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ ያስተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (unsigned rate correction) እና ነጠላ ዋጋ ላይ ፍሉድ መጠቀም በጨረታ ተወዳዳሪነት ያሰረዛል።
  • በስራ ዝርዝር ላይ ነጠላ ዋጋ አለመሙላት (un filled rate ) ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል።
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጫራቾች ጨረታውን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ በአካል በመቅረብ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውን (ኦርጅናል) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) ለአንድ የጨረታ ሰነድ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻን።
  • ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 8ተኛው የመቁጠሪያ ቀን (calendar days ) ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት መገናኛ አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ መስሪያ ቤት ለዚህ በተዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል

ማሳሰቢያ ፡- ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 8ተኛው የስራ ቀን በአል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን 4 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በዚሁ ሰዓት 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።

አድራሻ፡- በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 በተለምዶ ከለም ሆቴል ወደ 24 በሚወስደው መንገድ ላይ ሲድራ ሆቴል ፊት ለፊት ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር መረጃ፦ +251 91 163 5081 / +251 91 068 1737


Tender details

  • Deadline: 2026-05-20
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 8ተኛው የመቁጠሪያ ቀን (calendar days ) ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-05-20 10:30
  • Bid opening (note): ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 8ተኛው የመቁጠሪያ ቀን (calendar days ) ጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: አባተ እና ትህትና ሪል እስቴት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር
  • Buyer address: በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 በተለምዶ ከለም ሆቴል ወደ 24 በሚወስደው መንገድ ላይ ሲድራ ሆቴል ፊት ለፊት ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ
  • Bid bond: 20%
  • Bid document price: 1,000.00 ብር ለአንዱ ሰነድ
  • Published: May 13, 2026
  • Posted at: 2026-05-13T09:57:32.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders