ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን በሁሩታ፣ ዲክሲስ፣ ጎንዴ፣ መቂና በገላን የሕንጻ ማሳመር ሥራ፣ የጥበቃ ቤት፣ ደረቅ ሽንት ቤትና የአጥር ሥራ በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን በሁሩታ፣ ዲክሲስ፣ ጎንዴ፣ መቂና በገላን የሕንጻ ማሳመር ሥራ፣ የጥበቃ ቤት፣ ደረቅ ሽንት ቤትና የአጥር ሥራ በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
RFQNo. 4283724, 4283801, 4283786, 4283770, እና 4283800 ቅደም ተከተል ።
በዚሁ መሠረት በግንባታ ዘርፍ የተሰማራችሁ፣ሕጋዊ የታደሠ ፍቃድ ያላችሁና ቢያንስ ሁለት ዓመት የሥራ ልምድ ያላችሁ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ደረጃ GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ኮንትራክተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማኅበር ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሥሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።
መስፈርት
1. ጨረታው ከግንቦት 09 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፤
2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሠ የንግድ ፈቃድ፣ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በግንባታ ዘርፍ የሠሩበትን የሥራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 25,000.00/ ሃያ አምስት ሺህ/ የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ሲ.ፒ.ኦ በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
6. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለዉ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም።
7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል።
8. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘገጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-111-0994 / 022-112-1660 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን
Tender details
- Deadline: 2026-06-02
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-06-02 14:00
- Region: Oromia
- Publishing entity: Ethio Telecom
- Buyer TIN: 0036917337
- Buyer address: addis ababa
- Bid bond: 25,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: May 14, 2026
- Posted at: 2026-05-14T08:41:40.000Z
- Buyer website: https://www.ethiotelecom.et
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.