የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የአስፋልት ዌሪንግ ኮርስ፣ አስፋልት ባይንደር ኮርስ እና ዲቢኤም ምርቶች በቁርጥ ዋጋ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል
Description
የአስፋልት ዌሪንግ ኮርስ፣ አስፋልት ባይንደር ኮርስ እና ዲቢኤም ምርቶች የቁርጥ ዋጋ ግዥ ጥሪ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለ2018 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚያከናውነው የመንገድ ግንባታ ስራ ግብዓት የሚያገለግሉ የአስፋልት ዌሪንግ ኮርስ፣ አስፋልት ባይንደር ኮርስ እና ዲቢኤም ምርቶች በቁርጥ ዋጋ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የምርቱ ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
የአንድ ቶን ነጠላ ዋጋ ትራንስፖርት +ተ.እ.ታ ጨምሮ በብር |
|
1 |
አስፋልት ዌሪንግ ኮርስ |
በቶን |
22,465.08 |
26,410.00 |
|
2 |
አስፋልት ባይንደር ኮርስ |
በቶን |
43,210.90 |
26,755.00 |
|
3 |
ዲቢኤም |
በቶን |
21609.48 |
24,800.00 |
- አግባነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ላይ መ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
- አቅራቢዎች የራሳቸው የሆነ የአስፋልት ማምረቻ ፕላንት ክሬሸርና የማምረቻ ኳሪ ሊኖራቸው ይገባል የባለቤትነት ማረገጋጫ ሰነድ ሊብሬ በውልና ማስረጃ የተመዘገበ ውክልና ወይም ለዚህ ቁርጥ ዋጋ ግዥ የአቅርቦት ጊዜ የሚሸፍን የኪራይ ውል ለውል ዘመኑ የሰነድ ማረጋጋጫ መቅረብ አለበት።
- የሚቀርበው ምርት በባለስልጣን መ/ቤቱ የጥራት መመዘኛ መስፈርት /specification/ መሰረት መሆኑ መ/ቤቱ በላብራቶሪ የጥራት ፍተሻ ያከናወናል።
- አቅራቢዎች በሁለትና ከዚያ በላይ ምርቶችንየሚያቀርቡ ከሆነ በቀን ቢያንስለተዋዋሉባቸው ምርቶች በድምሩ 1000 ቶን ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን በአንድ ምርት ዓይነት ብቻ የሚዋዋሉ ከሆነ በቀን 800 ቶን በሚሰጣቸው የግንባታ ፕሮጀክቶች ድልድልና የአቅርቦት መጠን መሰረት በየፕሮጀክቱ አጓጉዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ባለስልጣን መ/ቤቱ በተ.ቁ. 4 የተቀመጠውን መጠን የአየር ንብረት እና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ከአቅም በላይ በሆነ ምከንያቶች ስራ ባይኖረው አለማዘዝ ወይም ቀንሶ ሊያዝ ይችላል።
- አቅራቢዎች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀን እና ሰዓት በባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 105 ከላይ የተገለፁትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
- አቅራቢዎች በሚዋዋሉት መጠን መስረት ለ1 ሳምንት የሚሆን አስፋልት ሚክስ ለማምረት የሚያስችል ቢቱሜን ግብዓት ያላቸው መሆኑን ለምዝገባ ሲመጡ በጽሑፍ ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
- የማምረት አቅማችሁን ባለስልጣን መ/ቤቱ የሚያረጋግጥ ሲሆን ቅድሚያ ለመጣ እና የተጠየቁ መስፈርቶችን አሟልቶ ዉል ለመዋዋል ዝግጁ የሆነ ቅድሚያ ይሰጠዋል።
- ውል የተዋዋሉ አቅራቢዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ምርት አቅርቦት መጀመር አለባቸው።
- ከባለስልጣን መ/ቤቱ ጋር ላለፉት 2 ዓመታት ውል ኖሯቸው የውል አፈጻጸማቸው ከ80% በታች የሆኑ አቅራቢዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- አቅራቢዎች ከባለስልጣን መ/ቤቱ ፍላጎት ከ25% በታች ውል ለማዋዋል ቢቀርቡ ማቅረብ አይችሉም።
- በአገር አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ በ10% ሲጨምር ወይም ሲቀንስ ለአንድ ቶን ለማምረቻ የሚያስፈልግ የነዳጅ 16.25 ሊትር በሚደረግ የውል ቀመር ልዩነቱን መሰረት በማድረግ የዋጋ ማስተካከያ ይደረጋል።
ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የግዥ ፍላጎቱን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ 011-372-2815/ 011 371-4103
ሳርቤት ፑሽኪን አደባባይ አጠገብ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን
Tender details
- Deadline: 2026-06-01
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
- Bid opening: 2026-06-01 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Roads Authority
- Buyer address: አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ሳር ቤት ፑሽኪን አደባባይ ሳይደርስ
- Published: May 14, 2026
- Posted at: 2026-05-14T09:08:48.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.