ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን በሪጅኑ ሥር የተለያዩ ቦታዎች ላይ ያሉትን የማስታወቂያ ሥራዎችን በማስታወቂያ ዘርፍ የተሰማሩትን ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን በሪጅኑ ሥር የተለያዩ ቦታዎች ላይ ያሉትን የማስታወቂያ ሥራዎችን በማስታወቂያ ዘርፍ የተሰማሩትን ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
RFQ No. 4283857
በዚሁ መሠረት በማስታወቂያ የሥራ ዘርፍ የተሰማራችሁ፣ ሕጋዊ የታደሰ ፍቃድ ያላችሁና ቢያንስ አንድ ዓመት የሥራ ልምድ ያላችሁ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 25 ቀን 208 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማኅበር ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሥሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን
መስፈርት
1. ጨረታው ከግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፤
2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በማስታወቂያ ዘርፍ የሠሩበትን የሥራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ/ የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ሲ.ፒ.ኦ በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትከክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
6. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል።
8. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-111-0994 / 022-112-1660 ደውሎ መጠየቅ
ኢትዮ ቴሌኮም
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን
Tender details
- Deadline: 2026-06-02
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-06-02 14:00
- Region: Oromia
- Publishing entity: Ethio Telecom
- Buyer TIN: 0036917337
- Buyer address: addis ababa
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: May 15, 2026
- Posted at: 2026-05-15T07:24:41.000Z
- Buyer website: https://www.ethiotelecom.et
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.