የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ፋይናንስ ጽ/ቤት የሰራተኞች ክበብ በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር 003/2018
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ፋይናንስ ጽ/ቤት በስሩ ላሉት ጽ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸው
- ሎት 1 የሰራተኞች ክበብ በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. ከላይ በተራ ቁጥር ለተጠቀሱት አግባብነት ያለው ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የምዝገባ ወረቀት ቲን ነበር ቫት ወይም ቲኦቲ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
2. ከመ/ቤቱ የሚቀርብለት ቤት ውሃ፣ መብራት፣ ፍሪጅ፣ የሻይና ቡና ማሽን፣ ኦቭን፣ ወንበር እና ቴሌቭዝን የሚያቀርብ ይሆናል። ሌላ ለክበቡ የሚያስፈልገውን DSTV ጨምሮ በዋጋ አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ የሚያሟላ ይሆናል።
3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት አስኮ ጨረታን አለፍ ብሎ ፖሊስ ጣቢያ ጀርባ በሚገኘው የጉለሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት የፋይናንስ ግዥ አስተዳደር 3ኛ ፎቅ በመገኘት የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ የኢትዮጵያ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱ መውሰድ ትችላላችሁ።
4. ተጫራቾች የእያንዳንዱን ዋጋ ቫትን ወይም ቲኦቲን አካቶ በመግለጽ የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በሰነዱ ላይ እና ፖስታው ላይ ማህተም በማድረግ ማስገባት ያለበት ሲሆን ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር እና አንድ እቃ ላይ ሁለት ዋጋ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን።
5. የሚጫረቱበትን አድራሻቸውን ስልክ ቁጥር በመጥቀስ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
6. ለተጠቀሰው ሎት የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
7. የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ ጨረታው በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል።
8. ጨረታው በአስረኛው ቀን 10፡30 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ የሚከፈት ይሆናል ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት አስኮ ከጨረታ አለፍ ብሎ ፖሊስ ጣቢያው ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ ቢሮ ቁጥር 305 ላይ ይገኛል።
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 827- 8749 / 011 827- 8662
የጉለሌ ክፍለ ከተማ
ወረዳ 05 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-27
- Bid closing time: 16:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን 10፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-28 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን 10፡30 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ 4፡00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Gulele Sub City Woreda 5 Administration Finance Bureau
- Bid bond: 5000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: May 16, 2026
- Posted at: 2026-05-16T08:31:56.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.