በጉ/ክ/ከተማ አዲስ ሕይወት ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት ሰርቨር ; EMR (Electro medical record) ከነ ዝርጋታው ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የሶስተኛ ዙር ዕቃ ግዥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 003/2018 ዓ.ም
በጉ/ክ/ከተማ አዲስ ሕይወት ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት የሶስተኛ ዙር ሰርቨር ; EMR (Electro medical record ) ከነ ዝርጋታው ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ለዚህም፡-
- ማንኛውም ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው የቫት ተመዝጋቢ የሆነ የዘመኑን ግብር የከፈለና በአቅራቢዎች ሊስት የተመዘገበ በራሱ ትራንስፖርት ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ የሚችል።
2. ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ የዕቃውን ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 EMR/ሰርቨር ዕቃዎች 30,000 በጤና ጣቢያው ስም በሎቱ የተገለፀውን CPO (ሲፒኦ) ማቅረብ አለባቸው።
3. አሸናፊ ተጫራቾች ለውል ማስከበሪያ የሚውል የጠቅላላ ዋጋ 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ማንኛውም ተጫራች የዕቃዎቹን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ጤና ጣቢያው ድረስ በመምጣት አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 406 ግዥ ከፍል ሰነዱን መግዛት ይችላል። ሆኖም ግን በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ በዋስትና ደብዳቤ ሰነዱን በነፃ መውሰድ የሚችሉ ይሆንና ነገር ግን ድርጅታቸው በማያመርቱባቸው እቃዎች ሎቶች ላይ የጨረታ ሰነድ የሚገዙ እና የጨረታ ማስከበሪያ CPO(ሲፒኦ) ማቅረብ አለባቸው።
5. የጨረታ ሰነዱን የሚወዳደሩበትን ሎት ዋጋ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በየሎቱ ታሽጎ/ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን እስከ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው በ10ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ በ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ይከፈታል።11ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
7. የጨረታ ሰነዱን ዋጋ ሞልተው ለማስገባት ሲመጡ በቅድሚያ ናሙና መቅረብ ባለባቸው እቃዎች ላይ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
8. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረቱበትን እቃ መ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው አመቱን ሙሉ ማቅረብ የሚችል።
9. ጤና ጣቢያው የዕቃውን ብዛት እንደአስፈላጊነቱ ከውል በፊትም 20% እና ከውል ቡኃላ 25% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. መስሪያ ቤቱ የዕቃውን አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው እስከ 6 ወር ድረስ የእቃውን 25% በንጥል ዋጋ ተጨማሪ ግዥ ትዕዛዝ ሰጥቶ ግዥ መፈፀም ይችላል።
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ሽሮሜዳ ሥላሴ ቤ/ክርስቲያን ሳይደርሱ በስተግራ በሚያስገባው አስፓልት 500 ሜትር ገባ ብሎ በቀድሞው ቀበሌ 23/18 ባሁኑ ወረዳ 6 አጠገብ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 11 89 96 32/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በጉ/ክ/ከተማ የአዲስ ሕይወት ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-05-26
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-27 12:00
- Bid opening (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Gulele Sub City Addis Hiwot Health Center
- Buyer address: ሽሮሜዳ ሥላሴ ቤ/ክርስቲያን ሳይደርሱ በስተግራ በሚያስገባው አስፓልት 500 ሜትር ገባ ብሎ በቀድሞው ቀበሌ 23/18 በአሁኑ ወረዳ 6 አጠገብ
- Bid bond: 30,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: May 17, 2026
- Posted at: 2026-05-18T08:11:08.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.