በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በወረዳ 7 ለሚያሠራው የአስፋልት መንገድና ፍሳሽ መስመር ሥራ በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የግንባታ ሥራ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ህ/ተ/በ/ፍቃ/ማስ/ጽ/ቤት 007/2018
በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በወረዳ 7 ለሚያሠራው የአስፋልት መንገድና ፍሳሽ መስመር ሥራ በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን፣ የተሟላ የሰው ኃይል እና ማሽነሪዎች በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ሥራውን ማጠናቀቅ የሚችል በተጨማሪም የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
|
ሎት |
የሥራው ዓይነት |
የግንባታ ጊዜ (በቀን) |
ደረጃ |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን |
የጨረታ ሰነድ የሚገባበት ቀን |
የጨረታ መክፈቻ ቀን |
|
1 |
የአስፋልት መንገድ እና የፍሳሽ መስመር ስራ |
180 ቀን |
በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ ወይም በመንገድ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 2 እና ከዚያ በላይ |
ከታወቀ ባንክ የመጫረቻ ዋጋውን 1%(አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና |
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ በ16ኛው ቀን ከ2፡30-4፡00 ብቻ |
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ በ16ኛው ቀን 4፡30 ጀምሮ |
- ለሥራው ሕጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር (የ2017 ዓ.ም) የከፈሉ ፣ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ከፌዴራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር የብቃት ምስክር ወረቀት ያላቸው እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው (የሁለቱንም ብቃት ማረጋገጫ)፣ እንዲሁም በ2018 በጨረታ ለመሳተፍየሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው ሕጋዊ አካል ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የአቅራቢነት ምዝገባ (supply list) ያላቸው ፣
- ተጫራቾች ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ዘወትር በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አምስተኛ ፎቅ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውን (Original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) እንዲሁም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር፦1000029579467 ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የህ/ተ/በ/ፈ/ማ/ጽ/ቤት በማለት የማይመለስ 1000 /አንድ ሺህ ብር/ አስገብታችሁ ዋናውን /ኦሪጅናል የባንክ ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን ዘወትር 2፡30 እስከ 10፡30 ሰአት ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ሰነዶች አንዱን ያጓደለ ሰነድ መውሰድ አይችልም።
- ተጫራቾች የጨረታው ውድድር ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ስለሚኖረው ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሺያል ሰነድ፣ አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ በማሸግ በድምሩ ስድስት ሰነድ ለየብቻ በታሸገ በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ፊርማ፤ ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND or BID SECURIY) ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ማህተም፤ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ በተጨማሪም የታሸገውን ፖስታ የፋይናንሺያል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግ ቴክኒካል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግ እንዲሁም ሁለቱን ፖስታ (የፋይናንሺያል እና ቴክኒካል) እና የCPO ፖስታውን በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ከም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ስአት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይንም ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች ለ90 ቀናት የሚያገለግል ወይም የሚቆይ የጨረተ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND or BID SECURIY) በባንክ ትእዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /UNCONDITIONAL BANK GUARANTEE በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበርያ ጽ/ቤት ስም የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ያላገናዘበ እጅግ የተጋነነ ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ ማለትም የሚሠራውን ሥራ ያላማከለ ከሆነ ተጫራቹ የዋጋ ትንታኔ (Cost Break down) ከተገቢው መረጃ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም የቀረበው ዋጋ ከሥራው ጋር ያልተመጣጠነ (unbalanced Bid) ከሆነ ተጫራቹ ከጨረታ ውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የተጫራቾች መመሪያን በሚያዘው መሠረት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ሰነዱን ከላይ በተጠቀሰው በ16ኛው የስራ ቀን በቦሌ ክ/ከተማ ኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት ብቻ ማስገባት ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት የተጫራቾች መመሪያን እንዲያነቡና የሚሠራበትን ቦታ እንዲያዩ ይመከራል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ባለሙያዎች በድርጅታቸው ውስጥ ብቻ የሚሠሩ ወይም ለድርጅቱ ብቻ የፈረሙ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ በድርጅቱ ኃላፊ ወይም ተመሳሳይ ተግባር እና ሥልጣን በተሰጠው አካል እና በተቀጣሪው (በፈራሚው) ባለሙያ የተፈረመ ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡አንድ ባለሙያ ለሁለት እና ከዚያ በላይ ድርጅቶች ፈርሞ ከተገኘ ሁለቱም ድርጅቶች ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናል።
- በተጨማሪም የትኛውንም ከላይ የተዘረዘሩትን ሆነ በጨረታው ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ሕጎች አለማክበር በሚያስገቡት የመጫረቻ ሰነዶቻቸው በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ ፣ በሥራ ዝርዝርበሙሉም ሆነ በአንድ የሥራ አይነት ላይ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate)ሥራውን በነፃ እንደሚሠራ ይቆጠራል እንዲሁም በዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (Unsigned Rate Correction) እና በዋጋ ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Rate Correction) ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል።
- የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በክፍለ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አምስተኛ ፎቅ በአካል በመቅረብ መረዳት ይቻላል።
አድራሻ፡- መገናኛ አካባቢ የሚገኘው የክፍለ ከተማው ሕንፃ በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አምስተኛ ፎቅ
በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-01
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ በ16ኛው ቀን ከ2፡30-4፡00
- Bid opening: 2026-07-01 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ በ16ኛው ቀን 4፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 1000.00 ብር
- Published: May 17, 2026
- Posted at: 2026-05-18T08:41:42.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.