ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. የውስጥ ማስዋብ የማጠናቀቂያ ሥራዎች/ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት/መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ከዚህ በታች በቀረበው መሠረት፣ የውስጥ ማስዋብ የማጠናቀቂያ ሥራዎች/ዕቃዎች፣ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት/መግዛት ይፈልጋል።

.

ዓይነት

የጨረታ ቁጥር

የጨረታ ማስከበሪያ (ብር)

1

የህንጻው የውስጥ ክፍሎች ዲዛይንና ማስዋብ ሥራዎች (Interior Design Works)

17/2018

150,000

2

የሠራተኞች ካፍቴሪያ ዲዛይንና ግንባታ የውስጥ ማስዋብ ሥራ

18/2018

50,000

3

የጽሕፈት እቃዎች (ቶነር 151)

19/2018

20,000

4

የሠራተኞች የደምብ ልብስ

20/2018

20,000

ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው፡-

1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና ብቁ ልምድ ያላቸው።

2. ተጫራቾች ከግንቦት 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋናው መ/ቤት (ብሔራዊ ቲአትር አካባቢ) ሀብት ሥራ አመራር መምሪያ (22ኛ ፎቅ) በመምጣት ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 400.00 በመክፈል ስለ ጨረታው የሚገልፀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ከላይ ለእያንዳንዱ በሠንጠረዡ በተገለፀው መሠረት በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከሚጫረቱበት ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የመጫረቻ ሰነድ እና ዋጋ በኤንቬሎፕ በማሸግ እስከ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጧቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ የኩባንያው ዋና መ/ቤት 22ኛ ፎቅ ላይ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው በዕለቱ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጧቱ 3፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

6. ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፦ ናይስ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋና መ/ቤት (ብሔራዊ ቴአትር ጀርባ) ሀብት ሥራ አመራር መምሪያ (22ኛ ፎቅ)

የስልክ ቁጥር፡- 0911 430 292 / 0910 068 772

አዲስ አበባ።


Tender details

  • Deadline: 2026-05-30
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid opening: 2026-05-30 09:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Nile Insurance Company S.C.
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ ጥቅል
  • Published: May 17, 2026
  • Posted at: 2026-05-18T11:58:49.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders