ራሚስ ባንክ አ.ማ. ንብረት ባለበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ራሚስ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር (ፋይናንሲንግ) በዋስትና የያዘዉን በሰንጠረዡ ላይ የተጠቀሰውን ንብረት ባለበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም
|
የንብረት አስያዥ ስም |
ለጨረታ የቀረበው ንብረት ዓይነት |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ
|
የጨረታዉ ቀን፣ ሰዓት እና ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ
|
ጨረታው የወጣው |
||
|
ከተማ፣ ክ/ከ/ ወረዳ/ ቀበሌ |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ቁጥር |
የቦታ ስፋት በካ.ሜ/ሄክታር |
||||||||
|
1 |
አቶ ሚካኤል አክሊሉ አየለ |
አቶ አቡሽ ተፈራ ሙሉጌታ |
የንግድ (ኢንዱስተሪ) እስቶር፣ |
ፊንፊኔ |
በአዳማ ከተማ፣ ቦሌ ክ/ከተማ፣ ጎሮ ወረዳ |
OR001050138001 |
925.71 |
29,006,827.20 |
በ10/10/2018 ዓ.ም ከ4:00-5:00 አዳማ ከተማ ፍራንኮ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ አባገዳ ቅርንጫፍ ውስጥ |
ለሦስተኛ ጊዜ |
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ/ሲ.ፒ.ኦ በራሚስ ባንክ አ.ማ ስም አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ከጨረታው መጠናቀቅ በኃላ ወድያውኑ ይመለስላቸዋል።
- ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል፡፡ ባለ ዕዳዎቹ እና ታዛቢዎች ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል።
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝግያ ስዓት 5 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል። የጨረታ መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ አስኪለይ ድረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል። በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከባንኩ ህግ አገልግሎት ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ያሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% ጨምሮ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ የሊዝ ክፍያ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የስም ማዘወሪያ እና ማናቸዉም ከጨረታው ጋር በተገናኘ መንግስት የሚጠይቀው ክፍያ ይከፍላል። ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
- ውዝፍ የሊዝ ክፍያን በተመለከተ ከእዳ ተመላሽ ብር ካለ ከተመላሽ ብር ላይ የሚከፈል ሲሆን ተመላሽ ብር ከሌለ ግን የንብረቱ ጨረታ አሸናፊ ውዝፍ የሊዝ ክፍያን ሙሉ በሙሉ የሚከፍል ይሆናል።
- በባንኩ የፋይናንሲንግ ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ፋይናንሲንግ ሊሰጥ ይችላል።
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረበውን ንብረቶች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ይችላሉ።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09–10–01–40–72/ 09–42–10–36–62 ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት፣ ወይም በ 09–10–73–87-00 የባንኩን ፋይናንሲንግ አፕሬዛልስ እና ፖርት ፎሊዮ ማኔጅመንት ክፍል እና በ 09–11–28–15–16 የባንኩን ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ራሚስ ባንክ አ.ማ.
Tender details
- Deadline: 2026-06-17
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-06-17 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Rammis Bank
- Bid bond: 25%
- Published: May 17, 2026
- Posted at: 2026-05-18T13:27:35.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.