በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የICT እና ኢንተርኔት እቃዎች እንዲሁም የተሽከርካሪ ጎማዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የብሄራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር አብክመ/ኢቴቢ/ግ/ጨ/06/2018

በአማራ ብሔራዊ  ክልላዊ መንግስት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1) የICT፣ እና ኢንተርኔት እቃዎች
  • ሎት 2 ) የተሽከርካሪ ጎማዎች

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ህጋዊ ድርጅቶቹ በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

1. በዘመኑ የታደሰ አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።

2. የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4. የሎት፣ ተወዳዳሪዎች ከተ.ቁ 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከቴክኒካል ሰነዳቸው ጋር በአንድ ፖስታ በማሸግ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናቸውን ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር በሌላ ፖስታ በማሸግ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ብለው ለያይተው ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የሎት 2 ተወዳዳሪዎች ሙሉ መወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይችላሉ፡።

5. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 / ሁለት መቶ ብር / በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች ግዥ የሚፈጸምላቸውን እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ/specification/ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /BID BOND/የሚወዳደሩበትን ሎት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።

8. ጨረታው አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል።

9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ጨረታው አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት በቢሮ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 20 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10.ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8:00 ተዘግቶ በ8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 20 ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

11. አሸናፊው የሚለየው በጥቅል (በሎት) ዋጋ ይሆናል።

12. በአንድ ሎት ላይ በከፊል ዋጋ ሞልቶ መወዳደር ዋጋ ውድድር ውጪ ያደርጋል።

13. ተጫራቾች በዋጋ መሙያም ሆነ በቴክኒካል ሰነዳቸው ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ። አለማድረግ ከውድድር ውጪ ያደርጋል።

14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 5656 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ
ባህር ዳር


Tender details

  • Deadline: 2026-06-01
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጨረታው አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8:00
  • Bid opening: 2026-06-01 14:30
  • Bid opening (note): ጨረታው አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: May 18, 2026
  • Posted at: 2026-05-19T07:31:38.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders