የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ለማንቀሳቀስ የምርት መያዣ ፕላስቲክ ሳጥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር:- ኢ.ን.ሥ.ኮ ማዕከል ግዥ/ ብግጨ 06/2018
ኮርፖሬሽኑ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ለማንቀሳቀስ የምርት መያዣ ፕላስቲክ ሳጥን ግዥ የመንግስትን ማዥ መስፈርቶች የሚያሟሉ እና በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። የምርት መያዣ የፕላስቲክ ሳጥን ብዛት 10,000.00 (አስር ሺህ)
1. ተጫራቾች በዘርፋ ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ የድጋፍ ደብዳቤ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ስርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። እነዚህ ሰነዶች በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ሰነዶች ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያው ቀነ ገደብ በፊት ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታ መክፈቻው ቀን በኋላ የተገኘ ማስረጃ ተቀባይነት የለውም።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በመክፈል ከግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠቱ 2፡30 – 6፡30 እንዲሁም ከሰአት ከ7፡30 – 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡30 ድረስ ማመልከቻ በመያዝ ብሎክ 2 አንደኛ ፎቅ ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ። (አድራሻው ከስር ተገልጿል.)
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው. ኢንሹራንስ ቦንድና ቼክ ተቀባይነት የላቸውም። የጨረታ ማስከበሪያው በቴክኒካል ፐሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ወይም ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።
6. ተጫራቾች ቴክኒክ እና ፋይናንስ ሰነድ በግልጽ ከፍለው በተለያየ ኤንቨሎፕ ለየብቻ አሽገው ማቅረብ FOID ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
8. ከዋና የመወዳደሪያ ሀሳብ (ኦሪጅናል) በተጨማሪ የሚፈለጉ ኮፒዎች ብዛት 1(አንድ)
9. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ መጠን ለአሸነፉበት የምርት መያዣ ፕላስቲክ ሳጥን ጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ውሉን የሚፈፅሙ ይሆናል።
10. ተጫራቾች የምርት መያዣ ፕላስቲክ ሳጥን ናሙና መቅረብ አለበት።
11. ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን
የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
ደብረዘይት መንገድ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርጫፍ ፊት ለፊት
ፖ.ሳ.ቁ. 7858
ስልክ ቁጥር 011 416 7345/ 011 466 9336
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-05-27
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-05-27 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Trading Businesses Corporation
- Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
- Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: May 18, 2026
- Posted at: 2026-05-19T07:40:22.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.