በሀዋሳ ከተማ አስ/ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኤሌክትሪክ ኬብሎችና ብሬከሮች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና /ኢኮ/ልማት መምሪያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ በተለያዩ ከ/ ከተሞች ውስጥ ለመንገድ ዳር መብራት ጥገና አገልግሎት የሚሆኑ ኤሌክትሪክ ኬብሎችና ብረከሮች ግዥ በ2018 በጀት ዓመት በታቀደው መሠረት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ በዘርፉ ፈቃድ ካለው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት:
1. በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ᎒ -
2. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ ፣
4. በጨረታው እንዲሳተፍ የታከስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤
5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ በብር 300(ሶስት መቶ ብር) በመግዛት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000/አምሳ ሺህ ብር ብቻ/በባንክ የተረጋገጠ የተመሰከረ ሲፒኦ cpo ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰንድ ጋር ማቅረብ አለበት
7. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ እና ከላይ የተጠቀሱትን ቴክኒካል ቅድመ ግምገማ ሰነዶችን አሟልቶ በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10/አሥር ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል። የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁፕር 046-212-1334
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና /ኢኮ/ል/መም/ያ
ሀዋሳ
Tender details
- Deadline: 2026-05-28
- Publishing entity: Hawassa City Administration Finance & Economic Development Bureau
- Bid bond: 50,000 (አምሳ ሺህ ብር)
- Bid document price: 300 (ሶስት መቶ ብር)
- Published: May 19, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.