የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ንብረቶችን መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ስማቸው ከዚህ በታች የተመለከቱት ድርጅቶች በግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 1268/2014 አንቀጽ 12 መሰረት ከሠራኛው መደበኛ የወር ደመወዝ ላይ ተገቢውን የጡረታ መዋጮ ቀንሰው እና የድርጅቱን ድርሻ መዋጮ ጨምረው ለግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ፈንድ ገቢ ባለማድረጋቸው አስተዳደሩ በአዋጅ ቁጥር 1268/2014 አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 13 በተሠጠው ሥልጣን እና አዋጁን ለማስፈጸም በወጣው መመሪያ ቁጥር1086/2017 መሠረት የድርጅቶቹን ሀብት በግልጽ ጨረታ በመሸጥ ውዝፍ ጡረታ መዋጮ ዕዳው እንዲሰበሰብ ወስኗል።
በዚሁ መሠረት:-
|
ተራ |
ውዝፍ የጡረታ መዋጮ ዕዳው |
በቀጣይ የሚታሰብ ወለድ እና ቅጣት ሳይጨምር |
የካርታ ቁጥር የሊዝ |
የቦታ ስፋት በካሬ |
የድርጅቱ ሀብት |
የጨረታ መነሻ |
|
|
1 |
ኤም.ኤ.ቢጂ ትሬዲንግ ኃ/የተ/ የግ/ ማ |
15,950,806.59 |
751/2011 |
7,517.95 |
ሚዛን ተፈሪ ከተማ ሰፈር -5 ብሎክ 3 |
68,961,970.72 |
|
|
2 |
አኳድሬ የተጣራ |
7,744,514.28 |
መል/ሊ/0008 |
ከ500 ካ/ሜ |
ድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 09 |
51,225,932.57 |
|
|
3 |
አዲስ አበባ ቆዳ አ/ማህበር |
9,598,398.25 |
ለ.ዘ/ደ/215/19989/01 |
2003 |
አዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ወረዳ 14 |
69,899,284.00 |
|
1. ስለሀብቱ አሻሻጥ ከአስተዳደሩ የግዥ ዳይሬክቶሬትወይም ከሕግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት መረጃ ማግኘት ይቻላል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ብር 200.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ በግልጽ በማስፈር በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ አድርገው አድራሻው ለግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና መ/ቤት በማለት አስፍረው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሠዓት እንዲሁም ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በግዢ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው የግልጽ ጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
4. ተጫራቾች በቅድሚያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/10ኛውን በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለባቸው።
5. ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሠዓት ተዘግቶ በ4፡15 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስተዳደሩ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን የእረፍት ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት የሚከፈት ይሆናል።
6. ተጫራቾች ይዞታውን በግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ዋና መ/ቤት በሚያመቻቸው ፕሮግራም በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
7. አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዥው ዋጋ ጋር ታስቦ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ በመከፈል ሀብቱና መረከብ አለበት።
8. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ የማይከፍል ከሆነ ለጨረታው በዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ለአስተዳደሩ ገቢ ሆኖ የጨረታው አሸናፊነቱ ይሠረዛል።
9. ከሽያጩ ጋር በተያያዘ የሚከፈሉ ግብርና ታክሶች፣ የስም ማዛወሪያ እንዲሁም ሌሎች ማናቸውም ሕጋዊ ወጪዎች በገዢ ይሸፈናሉ።
10. አስተዳደሩ ስለሀብቱ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- መገናኛ ቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ፊት ለፊት
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-011 157 0333/ 011 157 4906
የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
Tender details
- Deadline: 2026-06-05
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-06-05 12:00
- Bid opening (note): ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡15 ሠዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Private Companies Employees Social Security Agency
- Buyer address: መገናኛ ከቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፊት ለፊት ወይም ከሙሉጌታ ዘለቀ ህንጻ አጠገብ
- Bid bond: 10%
- Bid document price: ብር 200.00
- Published: May 19, 2026
- Posted at: 2026-05-19T11:54:05.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.