እንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል የሲቲስካን ክፍል የሪኖቬሽን ስራ ደረጃ 6 እና በላይ የሆኑ ተጫራቾችን እና የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳድር ዞን የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት

  • ሎት 1. የሲቲስካን ክፍል የሪኖቬሽን ስራ ደረጃ 6 እና በላይ የሆኑ ተጫራቾችን እና
  • ሎት 2. የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
  1. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ በዘርፉ ህጋዊ የሆኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸዉ።
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት እና ከመንግስት የሚጠበቅባቸዉን የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸዉ ማስረጃ የግብር ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸዉ።
  3. የግዥዉ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸዉ።
  5. ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 3 መዉሰድ የሚቻል ሲሆን ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛዉ ቀን ድረስ እስከ 11፡30 ብቻ ማግኘት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በልዩ ልዩ ምክንያት በሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ያልታገዱ መሆን ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸዉን በአማርኛ ቋንቋ ማንኛውንም የመንግስት ግብር ያካተተ ሆኖ የጨረታ ሰነዱ በፖስታ ታሽጎ የድርጅቱ ክብ ማህተም፣ ፊርማ እና አድራሻ ማስቀመጥ አለባቸዉ፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ሥርዝ ድልዝ ማድረግ የለባቸዉም፡፡ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች የጨረታማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ማንኛዉንም የመንግስት ግብር አካቶ የሞሉትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ገቢ በማድረግ ከፖስታው ውስጥ አብሮ ማስገባት አለባቸዉ።
  9. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸዉ ከታወቀ ማንኛዉንም የመንግስት ግብር አካቶ የሞሉትን ጠቅላላ ድምር አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ማስያዝ አለባቸዉ።
  10. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ይቆይና በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሆነ ባይገኙ ፕሮግራሙ የማይስተጓጎል ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  11.  ሆስፒታሉ አሸናፊዉን በሎት የሚለይ ይሆናል።
  12. ተጫራቾች የተጠየቁ እቃዎችን ሆስፒታሉ በጠየቀዉ (ስፔስፊኬሽን) መሰረት በራሳቸው ወጭ እስከ ሆስፒታሉ ድረስ በማምጣት የሚያስረክቡ ይሆናል።
  13.  መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ 058 827 04 27 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።

የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-06-02
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ይቆይና በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-02 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ይቆይና በ16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Injebara General Hospital
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published: May 18, 2026
  • Posted at: 2026-05-21T09:01:25.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders