የምሳሌ አባዶ ከብሎክ 440 እስከ 447 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማህበር በግቢ ውስጥ ያሉትን 8 የጋራ መኖሪያ ህንፃዎች፣ የጋራ መጠቀሚያ(ኮሚናል) እንዲሁም የጥበቃ ቤት የህንፃ ቀለም ቅብ ስራ እና የጥገና ስራ በዘርፉ በተሰማሩ ባለሙያዎች በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Description
ምሳሌ አባዶ ከብሎክ 440 እስከ 447 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
ቀን፡ 14/09/2018 ዓ.ም
የምሳሌ አባዶ ከብሎክ 440 እስከ 447 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማህበር በግቢ ውስጥ ያሉትን 8 የጋራ መኖሪያ ህንፃዎች፣ የጋራ መጠቀሚያ(ኮሚናል) እንዲሁም የጥበቃ ቤት የህንፃ ቀለም ቅብ ስራ እና የጥገና ስራ በዘርፍ በተሰማሩ ባለሙያዎች በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
ጨረታውን ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፦
1.በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያለው
2. የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ ማረጋገጫ ያለው
3. የታደሰ የአዲስ አበባ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
4. በተመሳሳይ የስራ መስክ ሶስት እና ከዚያ በላይ የተለያዩ ሳይቶች ላይ የሰራበትን የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችልና ሳይቱን የሚያስጎበኝ
5. ማንኛውም ተጫራች ከላይ የተዘረዘሩትን ስራዎችን ለመስራት በማህበሩ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት ከብሎክ 440 እስከ 447 ያሉ ብሎኮችን በመመልከት የመስክ ምልከታ ወይም የሚሰራውን ስራ በመጎብኘት አለበት ወይም የስራ ልኬት መውሰድ አለበት
6. ማንኛውም ተጫራች ዝርዝር ስራዎቹን የአንድ ነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ማቅረብ አለበት፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 40,000(አርባ ሺህ ብር) አሰርቶ ማቅረብ አለበት፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከማህበሩ ጽ/ቤት ቢሮ የማይመለስ በ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመግዛት የሚሰሩበትን ዋጋ በግልፅ በኮምፒውተር በመፃፍ ማስገባት አለበት፡፡ በእጅ የተፃፈ እና ስርዝ ድልዝ ያለበት ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን ህጋዊ ማህተም በማድረግ በፖስታ በማሸግ የጨረታ ሰነዱ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በተቀመጠው ቀን በማህበሩ ጽ/ቤት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን
- ጨረታው እሁድ ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በዛኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ይዘው በተገኙበት ይከፈታል።
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ
- ለሚ ኩራ ክተማ ወረዳ 14 የካ አባዶ 13 በተለምዶ ፒያሳ አካባቢ 440-447 ቅጥር ግቢ ውስጥ እንገኝለን ።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር
- +2519-73-87-64-34 / +2519-12-44-41-30.
Tender details
- Deadline: 2026-05-31
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-05-31 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ምሳሌ አባዶ ከብሎክ 440 እስከ 447 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማህበር
- Bid bond: 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር)
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
- Published: May 22, 2026
- Posted at: 2026-05-22T07:22:48.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.