የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተለያዩ ማሽነሪዎች እና ተሽከርካሪዎች የኪራይ አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ 21/2018

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የሚከተሉትን የማሽነሪዎች ከዚህ በታች በሎት ተከፍሎ በተቀመጠው መሰረት በጨረታ አወዳድሮ ከ6 ወር ያላነሰ ጊዜ ውል ፈፅሞ ለመስራት ፍላጎት ካለው ድርጅት ጋር የኪራይ አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

  • ሎት 1፡-የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ኪራይ፣
  • ሎት 2 የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ኪራይ (ከባድ መኪና፣አይሱዚ እና pickup መኪና) እና
  • ሎት 3፡ ሌሎች ማሽነሪዎች(ሚክሰር፣ ቫይብሬተር፣ ጀኔሬተር፣ ውሃ ፓምፕ ፣ፕሌት ኮምፓክተር) ኪራይ አገልግሎት

ስለሆነም

1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ Ap የተሰጠ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀትና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (OCC) አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና (unconditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::

3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

4. የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን(OCC) አጠገብ ስልክ ቁጥር 09-20-11-75-60

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሸን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-05
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-06-05 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Administration Construction Design, Building and Consultancy Organization
  • Buyer address: አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ
  • Bid bond: እያንዳንዱ ሎት ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ) ብር
  • Published: May 24, 2026
  • Posted at: 2026-05-25T08:03:52.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders