የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የጥበቃ ሥራ፣ የፅዳት ሥራ እንዲሁም የግቢ ውስጥ እና አካባቢ አረንጓዴ ልማት እንክብካቤ ሥራ በ out source በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2019 የበጀት ዓመት ፦
1. የጥበቃ ሥራ
2. የፅዳት ሥራ
3. የግቢ ውስጥ እና አካባቢ አረንጓዴ ልማት እንክብካቤ ሥራ በ out source በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ።
- 2018 ዓ ም የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ በዘርፉ ያላችሁ እንዲሁም የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈለ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት (VAT) ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆን መረጃ ማቅረብ የሚችል፡
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባችሁን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ለፅዳት ሥራ ከአዳማ ከተማ የምግብ ዋስትና እና የሥራ ፈጠራ ከኅሎት / ከጥቃቅንና አንስተኛ ኢንተርፕራይዝ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት የሚችል እና በፅዳት ሥራ ላይ በ"IMX'' የተደራጁ መሆን አለባቸው።
- ለግቢ ውስጥ እና አከባቢ አረንጓዴ ልማት እንክብካቤ ሥራ ከአዳማ ከተማ የምግብ ዋስትና እና የሥራ ፈጠራ ክኅሎት ከጥቃቅንና አንሰተኛ ኢንተርፕራይዝ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት የሚችል እና በግቢ ውስጥ እና አከባቢ አረንጓዴ ልማት እንክብካቤ ሥራ ላይ በIMX'' የተደራጁ መሆን አለባቸው።
- ለጥበቃ ሥራ ከሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት የሚችል
- ከዚህ በፊት ከአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በሥነ ምግባርም ሆነ በሌላ ምክኒያት ደብዳቤ የተፃፈበት መወዳዳር አይችልም።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦሪጅናል ለየ ብቻ በተለያየ ፖስታ ማሸግ አለባቸው።
- ስርዝ ድልዝ ያለው ፣ የማይታይ የጨረታ ሰነድ ወይም የዋጋ ዝርዝር ተቀባይት የለውም።
- ጨረታውን ከአሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ የአሸኑፉበትን ዋጋ 10% ማስያዝ የሚችል።
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኮሌጁ ግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ክፍል ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ 500/አምስት መቶ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ አለባቸው።
- የፅዳት ሥራ ጨረታው የሚከፈተው በ03/10/2018 ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የጥበቃ ሥራ ጨረታው የሚከፈተው 04/10/ 2018 ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የግቢ ውስጥ እና አከባቢ አረንጓዴ ልማት እንክብካቤ ሥራ ጨረታው የሚከፈተው በ03/10/2018 ከቀኑ 9፡30 ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚሞሉትን ዋጋ በመሥሪያ ቤቱ ሰነድ ብቻ ላይ መሆን አለበት።
- ለጨረታው ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በ 'CBE, CBO, & Sinqe" ባንክ ብቻ ማሰያዝ የሚችል መሆን አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
የአዳማ ሆስፒታል
ሜዲካል ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-06-11
- Bid closing time: 15:30
- Bid closing (note): የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰአት አልተገለፀም
- Bid opening: 2026-06-11 15:30
- Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Oromia
- Publishing entity: Adama Hospital Medical College
- Bid bond: ለእያንዳንዱ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር
- Bid document price: ለእያንዳንዱ 500 (አምስት መቶ ብር)
- Published: May 26, 2026
- Posted at: 2026-05-26T08:30:28.000Z
- Buyer website: https://www.adamahmc.edu.et/
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.