ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ የተረፈ ምርት የእንጨት ፍቅፋቂ በግልፅ ጨረታ በቀን 9000 ኪግ ለ6ወር የሚቆይ ውል መዋዋል የሚችል አቅም ያለው አቅራቢ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የሳጋ ቱራ/የእንጨት ፍቅፋቂ / የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሆቡማማ/12/18
ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ የተረፈ ምርት የእንጨት ፍቅፋቂ በግልፅ ጨረታ በቀን 9000 ኪግ ለ6ወር የሚቆይ ውል መዋዋል የሚችል አቅም ያለው አቅራቢ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በሙሉ ከታች የተዘረዘሩትን በማሟላት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ቲን ቁጥር ያላቸው የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
2. ለጨረታው ሰነድ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ።
3. ለጨረታው ማስከበሪያ በሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር /HORIZON PLANATIONS PLC/ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲ ፒ ኦ /CPO/ 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ብቻ ከጨረታው ሰነድ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው።
4 በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀን አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ15ኛው ቀን በጨረታ ሰነዱ በሚገለፀው ቀን እና ሰዓት ይከፈታል።
5. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር በአካል በመገኘት የሳጋቱራውን ሳንፕል ማየት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የ ኪ.ግ ዋጋ ቫትን በመጨመር የሰራተኛ (ጫኝ እና አውራጅ) እንዲሁም የትራንስፖረት ዋጋ አካተው ድርጅቱ ድረስ የሚያቀረቡበትን ዋጋ መሙላት አለባቸው።
7.የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።
8.ጨረታው ከላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውበተገኙበት ይከፈታል።
9. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በተገለጸለት በ3 /ሶስስት/ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የሥራ ውል ተፈራርሞ ሥራውን መጀመር ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ ግን ከጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታው ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል።
10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 442 1238/ 09 86-12 48-55 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ፡- ቅ/ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደ ብሔረፅጌ መናፈሻ በሚወስደው መንገድ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ሆራይዘን
ሆራይዞን ፕላንቴሽን ኃላ.የተ.ያግል ማህበር ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-06-08
- Bid closing time: 23:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀን
- Bid opening: 2026-06-08 23:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በጨረታ ሰነዱ በሚገለፀው ቀን እና ሰዓት ይከፈታል
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Horizon Plantation P.L.C.
- Buyer address: ሳሪስ ቅ/ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደ ብሔረፅጌ መናፈሻ በሚወስደው መንገድ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
- Bid bond: 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: May 26, 2026
- Posted at: 2026-05-26T08:35:44.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.