በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን በ2018 በበጀት አመት ከሚያሰራቸው ፕሮጀክቶች መካከል በባ/ዳር ከተማ አስተዳደር ጣና መናሃሪያ ዝይን ሲራጅ ህንጻ፣ ቢላል ሱቅ-ፓፒረስ፣ ጋሳ ሆቴል-ኮበል መንገድ፣ አሮጌዉ ድልድይ ሰማታት፣ ኖክ ማደያ-ትራፊክ መብራት፣ እልልታ ሆቴል ቀኝና ግራ፣ ጣና የጥርስ ህክምና፣ አስፋዉ የጥርስ ህክምና፣ አዲስ አምባ ሆቴል ፊት ለፊት፣ ይቻላል ጸጉር ቤት፣ መርድ አ

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን በ2018 በበጀት አመት ከሚያሰራቸው ፕሮጀክቶች መካከል በባ/ዳር ከተማ አስተዳደር ጣና መናሃሪያ ዝይን ሲራጅ ህንጻ፣ ቢላል ሱቅ-ፓፒረስ፣ ጋሳ ሆቴል-ኮበል መንገድ፣ አሮጌዉ ድልድይ ሰማታት፣ ኖከ ማደያ-ትራፊክ መብራት፣ እልልታ ሆቴል ቀኝና ግራ፣ ጣና የጥርስ ህክምና፣ አስፋዉ የጥርስ ህክምና፣ አዲስ አምባ ሆቴል ፊት ለፊት፣ ይቻላል ጸጉር ቤት፣ መርድ አሊ ሱቅ፣ መታሰቢያ ህንጻ ፊትለፊት፣ ሳባ ካፌ፣ ዘይና ሲራጅ ህንጻ፣ ጂጂ ገበያ ማእከል ፊት ለፊት፣ ኤኤምኢ እንስሳት ህክምና ፊት ለፊት፣ ኢቲኤል መድሃኒት ቤት ያሉት ፕሮጀክቶች ላይ መሳተፍ ለሚፈልጉ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ 3 እና በላይ የሆኑ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

1. የታደሰ የንግድ የስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።

2. ከላይ  የተጠቀሰውን  ፕሮጀክት  ለማሰራት  አስፈላጊውን  ሁሉ  የሰው  ሃይል፣  የማቴሪያል  እንዲሁም የመሳሪያ አቅርቦቶችን  የሚያሳይ  በስማቸው የታሸገ  የፋይናንሽያል  እና  የቴክኒካል የመወዳደሪያ ሃሳቦችን  ማቅረብ አለባቸው።

3. የጨረታ  ሰነድ  መግዛት  የሚፈልጉ  ማንኛውም  ህጋዊ  ተጫራቾች  ባህር  ዳር  ከተማ  አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን የግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10  የማይመለስ ብር 2,000 (ሁለት ሽህ) በመክፈል መግዛት ምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

4. ማንኛውም  ተጫራች  የተጫራቹንና  የኘሮጀክቱን  ስም  በግልፅ  ተቀባይነት  ባለው  የጨረታ ማስከበሪያ  ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የጨረታ ዝርዝር መረጃ ሰንጠረዥ የተጫራቾች መመሪያ ተ.መ 21.1 ላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች መመሪያውን በማንበብ ሙሉ ፈቃደኛ እንዲሆኑ ይመከራሉ።

6. ኘሮጀክቶች የሚጠናቀቁበት ቀን በክፍል 8 አንቀጽ አ.ዉ.ሁ 72.1 ላይ በተገለጸዉ ቀን መሰረት ይሆናል።

7. ሁሉም የቅድመ ማጣሪያ ወይም ቴክኒካል እና ጨረታ ዋጋ ወይም ፋይናንሻል ሰነዶች በተለያዩ ኢንቨሎፓች ማህተም በማድረግ መታሸግ ይኖርባቸዋል፡፡(አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ)  ማድረግ አለባችሁ።

8. ጨረታው ሁለት የግምገማ ሂደቶች ይኖሩታል። የመጀመሪያው ሂደት የቴክኒካል ሰነዶች ግምገማ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ቴክኒካል ግምገማውን ካለፉት ተጫራቾች ውስጥ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ  በቁጥር  አብክመ  ገ/ቢ/ኮቢ-01/02፣ ግንቦት 15/2014 ዓም  በተሻሻለዉ መመሪያ መሰረት  የጨረታ  ዋጋ ያቀረበውን ተጫራች መምረጥ ይሆናል። ለበለጠ መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተያያዘዉን  መመሪያ በደንብ ማንበብ ይጠበቅባችኋል።

9. የታሸጉ የቅድመ ማጣሪያና የጨረታ ዋጋ ሰነዶች የሚቀርቡት ለመንገዶች ባለስልጣን የግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ሆኖ ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ከጠዋቱ  ከ2፡30 ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን ሳጥኑ እስኪታሸግ ድረስ ሲሆን ጨረታው  በይፋ  የሚከፈተው  ተጫራቾች  ወይም  ህጋዊ  ወኪሎቻቸው በተገኙበት፣  በ16ኛው  ቀን 3፡00  ታሽጎ 3፡30 ላይ በግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 14 ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፤ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከስራ ቀን ውጭ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።

10. ተጫራቾች ማንኛውንም ተጨማሪ መረጃ ከባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ስ.ቁ 058 320 1878 ማግኘት ይቻላሉ።

11. በባህር ዳር ከተማ ውስጥ በባለፈው አመት ውስጥ ፕሮጀክት ጀምሮ ያቋረጠ ወይም በተሰጠው ውል መሰረት ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ያሉት ተጫራች በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ አይችልም።

12. ማንኛውም ተጫራች ከስራ ዝርዝሩ ውስጥ ወይም ከዚህ በላይ የስራ አይነቶች ላይ የነጠላ ዋጋ ሳይሞላ ቢቀር ያለ ክፍያ ስራውን እንዲሰራ ይገደዳል።

13. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ከማስገባቱ በፊት የሳይት ጉብኝት ማድረግ ይጠበቅበታል። አሰሪ መስሪያ ቤቱ ከሳይቱ ሁኔታ ጋር የተያያዙ ቅሬታዎችን አይቀበልም።

14. ማንኛዉም ተጫራች በሚሞላዉ ሰነድ ላይ የሚፈጠር ስርዝ ድልዝ ከዉድድር ዉጭ የሚያስደርግ ይሆናል። ለበለጠ መደበኛ የጨረታ ሰነድ፣ ለግንባታ ሥራዎች ግዥ፣ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተዘጋጀ የ2011 ዓ.ም  መረጃ ከሰነዱ ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ይመልከቱ።

15. ተጫራቾች በ2016 ዓ/ም እና በ2017 ዓ/ም ከባ/ዳር ከተማ አስተዳደር የአስፓልት ጥገና ስራ የመልካም ስራ አፈጻጸም በቁጥር ቢያንስ አንድ ማቅረብ አለባቸው።

16. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአካል ወይም በወኪሎቻቸዉ አማካኝነት ሰነዱን መግዛት እንጅ በሶፍት ኮፒ በማንኛዉም ድህረ ገጽ መዉሰድ አይፈቀድም።

17.  ባለስልጣኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

18. ለበለጠ መረጃ ስልክ 058 320 1878 መደወል ይቻላል አድራሻ ባህር ዳር መንገዶች ባለስልጣን።

የባ/ዳር ከ/አስ/ መንገድ ባለስልጣን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-09
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 3፡00
  • Bid opening: 2026-06-09 15:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 3፡30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Bahir Dar City Administration Road Authority
  • Bid document price: 2,000.00 ብር
  • Published: May 25, 2026
  • Posted at: 2026-05-26T10:31:01.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders