የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የፅዳት አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/15/2018
የፅዳት የአገልግሎት ግዥ ለመፈፀም የወጣ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ208 በጀት ዓመት የፅዳት አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት (Specification) መሰረት አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ ማስረጃ፡የቫት ተመዝጋቢ፤ ቲን ማስረጃ መቅረብ ይኖርበታል ። እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ በሚገኘው ፋፋ የምግብ አማ ጀርባ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ግዥ ክፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ዋጋ ለ30 (ሰላሳ) ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል ፡፡ ጨረታው ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል ።
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
ስልክ +251 911 984 467 / +251 105 675 78
ፋክስ 0114 421 312
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-06-05
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-05 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Agricultural Business Corporation
- Buyer address: ከሳሪስ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ማህበር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
- Bid bond: 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር)
- Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: May 27, 2026
- Posted at: 2026-05-28T08:06:04.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.