ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የSage 50 Accounting 2024/2025 (20 Users – Quantum US Version) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የSage 50 Accounting 2024/2025(20 Users - Quantum US Version) ግዥ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፣LT/HT/H0/07/2026
- ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የSage 50 Accounting 2024/2025 (20 Users – Quantum US Version ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግንቦት 20 ቀን 2018ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 11 ቀን 2018ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-10፡00 ድረስ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:30-6:00“ሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ” ጠመንጃ ያዥ ንግድ ባንክ አጠገብ ቴሌ ጋራዥ ግቢ ውስጥ 2ኛ ፎቅ ቢሮቁጥር 211 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት፡-
- አንድ ዋና /Original የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ፣
- አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፣
- ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በሰም የታሸገ መሆን አለበት፣
- በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል። ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /CP.O/ ብቻ ለሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን ሰኔ 11 ቀን 2018ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 211 ሲሆን፣ ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ ቀን ሰኔ 11 ቀን 2018ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 211 ይሆናል።
6. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ያልተከተሉ ተጫራቾች ወዲያውኑ ከጨረታ ውድድሩ ውጪ እንደሚሆኑ እንገልጻለን።
7. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 68 13 56 75 ወይም 09 68 27 12 91 መጠቀም ይችላሉ።
8. ሕዳሴ ቴሌኮም ኤማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-06-18
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-18 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Hidase Telecom Share Company
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: May 27, 2026
- Posted at: 2026-05-28T09:17:01.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.