የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ጋምቤላ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ የእድሳት ሥራ ለማከናወን በግንባታ ሥራ ተቋራጭ የብቃት ማረጋገጫ ደረጃ Bc-4 Gc-4 እና ከዚያ በላይ ያሉትን የሥራ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ማሠራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ጋምቤላ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ የእድሳት ሥራ ለማከናወን በግንባታ ሥራ ተቋራጭ የብቃት ማረጋገጫ ደረጃ Bc-4Gc-4 እና ከዚያ በላይ ያሉትን የሥራ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ማሠራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
2. የታደሰ የብቃት ማረጋጫ ሰርተፍኬት ያለው፣
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
4. ከውዝፍ ግብር ነፃ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣
5. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያለው፣
6. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ14 ተከታታይ የሥራ ቀናት ተጫራቾች ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳ ቁጥር 1000067561647 ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን አድቫይስ አንድ ኮፒ ይዘው በመቅረብ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/አስ/ቡድን መሪ ክፍል መግዛት ይቻላል።
7. ተጫራቾች የጨረታውን ዋስትና ማስከበሪያ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በሲፒኦ ወይንም በባንክ ጋራንቲ ብቻ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች እድሳቱን የሚያከናውኑበትን ዋጋ ዋናውን እና ኮፒ 2 /ሁለት/ እና ካምፓኒ ፕሮፋይል ዋናውንና ኮፒ 2 /ሁለት/ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30-4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አስገብተው በዚሁ ቀን በ4፡50 ሰዓት ላይ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግዥና ፋይ/ አስ/ቡድን መሪ ክፍል ይከፈታል።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0475510548/0475510534 ይጠቀሙ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ጋምቤላ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-15
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30-4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-15 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡50 ሰዓት
- Region: Gambela
- Publishing entity: የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ጋምቤላ ጽ/ቤት
- Bid bond: 200,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: May 29, 2026
- Posted at: 2026-05-29T07:27:37.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.