በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጎፋ ዞን የሣውላ ማረሚያ ተቋም ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ እሰከ ሰኔ 30 ቀን 2019 ዓ/ም ድረስ ለ12 ወራት በህግ ጥላ ስር በመታረም ላይ ለሚገኙ ለህግ ታራሚዎች ምግብና አገልግሎት የሚውል እህል ማጣፈጫ ቅመማቅመም፣ ንፁህ የምግብ ዘይት፣ ስኳር እና የማገዶ እንጨት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጎፋ ዞን የሣውላ ማረሚያ ተቋም ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ እሰከ ሰኔ 30 ቀን 2019 ዓ/ም ድረስ ለ12 ወራት በህግ ጥላ ስር በመታረም ላይ ለሚገኙ ለህግ ታራሚዎች ምግብና አገልግሎት የሚውል፡- እህል ማጣፈጫ ቅመማቅመም፣ ንፁህ የምግብ ዘይት፣ ስኳር እና የማገዶ እንጨት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የቫቲ ተመዝጋቢ የሆነ፣ የግብር መለያ /Tin/ ቁጥር ያለው፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወርቀት ማቅረብ የሚችሉ።
2. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ፣ በCPO እና በጥሬ ገንዘብ የተረጋገጠ 25,000.00/ሃያ አምስት ሺህ ብር/ብቻ ማሳያዝ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሰውን ማስረጃዎችን እና የመጫረቻ ሠነድ ኦርጅናልና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ ውስጥ በማስገባት በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በመንግስት የሥራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
4. የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመንግሥት የሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ የማይመለስ 300/ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
5. ተጫራቾች ዕቃውን በራሳቸው ወጪ እስከ ሣውላ ማረሚያ ተቋም አምጥተው ማስረከብ አለባቸው።
6. የጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተገኙ ተጫራች የዕቃዎችን አጠቃላይ ዋጋ በ10% በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም /CPO/የዉል ማስከበሪያ በማስያዝ ከሣውላ ማረሚያ ተቋም ግዥ ፋ/ን/አስ/ር ደጋፊ ሥራ ሂደት ጋር የውል ስምምነት መፈፀም ይጠበቅባቸዋል።
7. ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ከሁሉም ዓይነት ናሙና ይዘው መቅረብ አለባቸው።
8. የጨረታ ማስታወቂያ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሳጥን 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ዕለቱ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። ዕለቱ ቅዳሜ፣ እሁድ እና በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በመንግሥት ሥራ ሰዓት ይከፈታል።
9. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መወዳደር ተቀባይነት የለውም።
10.ማረሚያ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ 09 16 87 73 79 / 09 13 88 73 30/
በጎፋ ዞን የሣውላ ማረሚያ ተቋም
Tender details
- Deadline: 2026-06-13
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሳጥን 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-13 12:00
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሳጥን 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Sawula Correctional Facility
- Bid bond: 25,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: May 29, 2026
- Posted at: 2026-05-29T07:50:32.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.