የኤጄሬ ማረሚያ ቤት ሐምሌ 01/2018 እስከ ታህሳስ 30/2019 ድረስ ለ6 ወር የሚቆይ በስሩ ለሚያስተዳድራቸው ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል የበሰለ ምግብ እና ያልበሰለ እህሎች፣ የማገዶ እንጨት፣ የማጣፈጫ ሸቀጣሸቀጥ ለሚያቀርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራትም ሆነ ድርጅት እንዲሁም ለህግ ታራሚዎች ምግብ ማብሰያ የማገዶ እንጨት፣ የማጣፈጫ ሸቀጣ ሸቀጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይ

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1

የኤጄሬ ማረሚያ ቤት ሐምሌ 01/2018 እስከ ታህሳስ 30/2019 ድረስ ለ6 ወር የሚቆይ በስሩ ለሚያስተዳድራቸው ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል የበሰለ ምግብ እና ያልበሰለ እህሎች፣ የማገዶ እንጨት፣ የማጣፈጫ ሸቀጣሸቀጥ ለሚያቀርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራትም ሆነ ድርጅት እንዲሁም ለህግ ታራሚዎች ምግብ ማብሰያ የማገዶ እንጨት የማጣፈጫ ሸቀጣ ሸቀጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማህበራትም ሆኑ ግለሰብ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያ ማሟላት አለባቸው።

1. በንግድ ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት። የግብር ከፋይነት (TIN NO ) ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም የቫት ከፋይነት እንዲሁም የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።

3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከወረዳው ማረሚያ ቤት መግዛት ይችላሉ።

4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡30 ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የህግ ታራሚዎች ኮሚቴ የማረሚያ ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ እና ከወረዳው አቃቢ ህግ ቢሮ እንዲሁም ከወረዳው ገ/ኢ/ትብብር በሚወከሉ በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን መስሪያ ቤቱ ዝ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።

5. ያልሆነ ነገር ካለ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ከታች በተገለፀው አድራሻችን ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ።

6. ተጫራቾች በጨረታ ሂደት ውስጥ ቅሬታ በበሰለ ምግብ አቅርቦት በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል። ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ለጨረታው ያቀረቡት ሀሳብ መቀየር ወይንም ማሻሻል እንዲሁም ከጨረታው እራስን ማግለል አይችልም።

7. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከታወቀበት አንስቶ በ3 ቀን ውስጥ ማረሚያ ቤት በመቅረብ ውል መፈረም ይኖርበታል ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ የመጠቀም መብቱ የተጠበቀ ነው። የበሰለ ምግብ ለማቅረብ ያሸነፈው ማህበር ወይም ግለሰብ ጥራቱን የጠበቀና ለአንድ ሰው የሚሆን ማረሚያ ቤቱ ባወጣው ሜኑ መሰረት አቅርቦት መመገብ አለበት።

8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በወረዳው ማረሚያ ቤት በዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

9. ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ የጨረታ ማስከበሪያውና የውል ማስከበሪያ በጥቃቅንና አነስተኛ ደንብ 192/2009 ተሻሽሎ በወጣው አንቀፅ 27 መሰረት ከአደራጁ ክፍል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው

10. ግለሰብም ሆነ ድርጅት ከሆኑ የጨረታ ማስከበሪያውን 2% በጥሬ ገንዘብ (በባንክ የተመሰከረለት сро ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።

11. ምግቡ የሚዘጋጀው በመስሪያ ቤቱ ማብሰያ ውስጥ ሆኖ በማብሰያ የሚያገለግሉ ዕቃዎች የማረሚያ ቤቱ እንዳለ ሆኖ የጎደለውን ጨረታውን ያሸነፈው ማህበራት ወይም ግለሰብ የማሟላት ግዴታ አለበት።

12. ተጫራቾች በጨረታው ሂደት ላይ ግልፅ ካላቸው ለማ/ቤቱ ለበላይ አካሎች ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት አንስቶ እስከ 5 ቀን ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ማቅረብ ይችላል።

13. መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ምዕ/ሸ/ዞን/ ኤጄሬ ማረሚያ ቤት ፋይናንስ ክፍል ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-283 0507

የኤጄሬ ማረሚያ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-18
  • Publishing entity: ኤጄሬ ወረዳ ማረሚያ ቤት
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published: Jun 01, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders