የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ንብረቶች በልዩ ድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለብድር ገንዘብ ማካካሻነት በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የመያዣ ንብረቶች በልዩ ድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው/የመያዣ ሰጪው ስም |
የንብረት አድራሻ |
የንብረት ዝርዝር |
የቦታ ስፋት (በሄክታር) |
የጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር) |
የጨረታ ሁኔታ |
የጨረታ ደረጃ |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|
1 |
አቶ ግርማ አፈወርቅ መድምም |
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስ/ላ/ክ ከተማ ወረዳ 08 |
ጋቴፕሮ ቆርቆሮ ፋብሪካ፣ የህንፃ ግንባታዎች፣ የኤሌክትሪክ ስራዎች፣ ማሽነሪዎች፣ ቁሳቁሶች፣ የቢሮ ዕቃዎችና መገልገያዎች፣ የጥሬ ዕቃና የምርት ክምችት |
1678 ካሬ ሜትር በሊዝ የተገኘ መሬት
|
122,600,997.28 (አንድ መቶ ሃያ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት ብር ከሃያ ስምንት ሳንቲም)
|
ልዩ ድርድር
|
አንደኛ
|
ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋት 4:00-6:00 ሰዓት
|
ማሳሰቢያ፤
1. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በፎርማቱ ላይ በመጥቀስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሁለተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ከሦስተኛው ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ሆኖ ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ተከፍቶ እስከ 6፡00 ሰዓት ይካሔዳል።
2. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
3. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡
4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ታወር ሁለት 5ኛ ፎቅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል። ህጋዊ ሰውነት ያላቸው አካላትን ወክሎ በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርብ ሰው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ/መተዳደሪያ ደንብ ከእነ ማሻሻያዎቹ (ካለ)፣ የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፍቃድ፣ ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን እና የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን ሰነዶችን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
5. 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ከፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል።
6. አንዳንድ የድርጅቶች ንብረቶች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል።
7. ተጫራቾች ንብረቱን ለመጎብኘት ከፈለጉ አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ቀን በፊት መጎብኘት ይችላሉ።
8. ባንኩ ንብረቱን የሚሸጠው ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ይሆናል።
9. የንብረቱ ስመ-ንብረት ለገዥው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል:: ገዥው ጉዳዩን ተከታትሎ ያስፈፅማል።
10. በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው።
11. በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦንጎይንግ ኮንሰርን ፕሮጀክትስ እና ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011524-53-73/011-524-42-69 ደውሎ ማግኘት ይቻላል። የመያዣ ንብረቶቹን መጐብኘት የሚፈልግ ከዳይሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል።
12. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
Tender details
- Deadline: 2026-07-06
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-07-06 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published: Jun 02, 2026
- Posted at: 2026-06-03T08:04:17.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.