የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለስካይላይት ሆቴል አገልግሎት የሚውል የሱፍ የምግብ ዘይት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:- SSNT-T620

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለስካይላይት ሆቴል አገልግሎት የሚውል የሱፍ የምግብ ዘይት ምርት ከሚያመርቱ ድርጅቶች ጋር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ስምምነት ለሶሥት (3) አመት ለመስራት ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-

  • በአገልግሎቱ ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ምዝገባ ወረቀት ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣ አንድ (1) ዓመት እና ከዚያ በላይ የሰራ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (ብር 100.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T620 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አንድ መቶ ሺህ ብር (100,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቛም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
  • ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሰነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እና የጨረታ ማስከበሪያ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል።
  • አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱየተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

ስልክ ቁጥር፡ 011-517-4552

አሊ አስፋው

ኢ-ሜይል:  AliAs@ethiopianairlines.com

Ethiopian


Tender details

  • Deadline: 2026-06-30
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid opening: 2026-06-30 15:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
  • Buyer TIN: 0000028498
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jun 03, 2026
  • Posted at: 2026-06-03T08:33:04.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders