ከነማ ፋርማሲ የመድሀኒት ቤት እድሳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቁ

ቁጥር 005/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያዋ ለሚገኙ ነዋሪዎች ለሁሉም ክ/ከተሞች ጤና መድህን ተጠቃሚዎች ለፌዴራል ጤና መድህን ተጠቃሚዎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ጥራታቸውና ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ መድሀኒቶች እና የህክምና መገልገያዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ በ53 መድሀኒት ቤቶች የዱቤ /credit እና የጥሬ ገንዘብ /cash ሽያጭ አገልግሎት እየሰጠ ያለ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው። ስለሆነም ድርጅቱ ከነማ ፋርማሲ የመድሀኒት ቤት እድሳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል መስፈርቱን የምታሟሉና ብቁ የሆናቹ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1. በንግድ ዘርፍ ወይም በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው እና የቲን ማስረጃዎች።

2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት (ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ) ጉለሌ ክ/ከተማ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS /ኤስኤም ኤስ ኤስ/ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

3. ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን 4፡30 ሰዓት የጨረታው ሳጥን የሚታሸግ ሰለሆነ አርፍዶ የሚመጣ ተቀባይነት የለውም። በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን በድርጅቱ ግዥ ዳይሬክቶሬት ክፍል 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 የሚከፈት ይሆናል።

ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

  • አድራሻ፡- ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS /ኤስ ኤምኤስ ኤስ / ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403
  • የስራ ሰዓት፡- ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት
  • ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0118-27-91-23

በመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር

ባለስልጣን የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-15
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-15 12:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kenema Pharmacy Enterprise
  • Buyer address: ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS (ኤስ ኤም ኤስ ኤስ) ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jun 03, 2026
  • Posted at: 2026-06-03T09:14:18.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders