የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ሳተላይት ካምፓስ እየተገለገለበት ያለውን የጂ+2 የአስተዳደር ህንጻ ለማደስ ተቋራጨችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ሳተላይት ካምፓስ እየተገለገለበት ያለውን የጂ+2 የአስተዳደር ህንጻ ለማደስ ተቋራጨችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

  1.  ሕጋዊ ምዝገባ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
  2. ደረጃቸው ቢሲ ጂሲ -5 እና ከዚህ በላይ ፍቃድ ያላቸው
  3. የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያደሱ ሆነው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ
  4. የዘመኑ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ።
  5. በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳደሪዎች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ተከታታይ 21ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 1000 አንድ ሺህ ብር በወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስም በተከፈተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ አካውንት ቁጥር 1000026941737 ገቢ በማድረግ ከኮሌጁ ግዥና ንብረት ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ሲያቀርቡ
    • ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸውን በሰም በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ ቴክኒካል በሚል በመለየት የጨረታ ማስከበሪያ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከኦርጅናል ቴክኒካል ዶክመንት ጋር በማድረግ
    • ለ/ ለፋይናንሺያል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ በሰም በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ ፋይናንሺያል በሚል በመለየት እስከ ተከታታይ 21ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስም እና ከቴክኒካል ዶክመንት ኦሪጅናል አብሮ መቅረብ አለበት።
  9. የጨረታው ቴክኒካል ዶክመንት በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  10.  የፋይናንሺያል የኘሮጀክቱ ግንባታ ዋጋ ከቴክኒክ ግምገማ ውጤት በኃላ የቴክኒክ ግምገማውን ያለፋት ተጫራቾች ሰነድ ብቻ የጨረታው ኮሚቴው በማስታወቂያ በሚገለፀው ቀን ይከፈታል።
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡-

1ኛ/ የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በሚከታተላቸው ፕሮጀክቶች በአፈፃፀማቸው ምክንያት 3ኛ ዙር ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መወዳደር አይችሉም።

2ኛ/ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ የሆነ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል፡-

ስልክ፡- 011-385-8463 ወልቂጤ

የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

እና ሳተላይት ካምፓስ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-27
  • Publishing entity: የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ሳተላይት ካምፓስ
  • Bid bond: 200,000.00 ብር
  • Bid document price: 1000.00 ብር
  • Published: Jun 07, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders