ስፋቱ 344.24 ካሬ ሜትር ቤትና ቦታ የሽያጭ ማስታወቂያ

Description

አማራ ክልል

  • አፈፃፀም ከሳሽ እነ ሀብተማርያም ደመላሽ/ 6 / ሰዎች
  • የአፈፃፀም ተከሳሽ እነ አዝመራ ደመላሽ / 2 / ሰዎች

መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ፤ በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 03 በምሥራቅ የባዘዘው በለጠ ቤት፣ በምዕራብ ጥላሁን ደጉ፣ በሰሜን መንገድ በደቡብ ጥሩ ማተቤ የሚያዋስኑትን ስፋቱ 344.24 ካሬ ሜትር ቤትና ቦታ በሟች አቶ ደመላሽ ካሳ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው ቤትና ቦታ በግልጽ ጨረታ በግምቱ መነሻ ዋጋ ብር 4,703,629.88 /አራት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ሃያ ዘጠኝ ብር ከሰማንያ ስምንት ሳንቲም/ ሆኖ ሐምሌ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ ጨረታ እንዲሸጥ የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ትዕዛዝ በሰጠው መሰረት የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ፀጥታውን የሚያስከብር ሁለት ባለሙያዎች እና የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፋሲሎ ክፍለ ከተማ አንድ ታዛቢ በመመደብ የጨረታው ስነ-ስርዓት በአግባቡ እንዲከናወን እንዲደረግ ሆኖ የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሐራጅ ባይም ጨረታውን በበላይነት በመምራት ጨረታው ይካሄዳል።

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ ማንኛውም ሰው ከቦታው በመገኘት ምልከታ አድርጐ ቀርቦ ህጋዊ መታወቂያ በመያዝ መጫረት መሳተፍ የሚቻል እና አሸናፊው እንደታወቀ ያሸነፈበትን ገንዘብ ከተቻለ ሙሉውን ገንዘብ የሚያስይዝ ካልተቻለም አንድ አራተኛውን ወዲያውኑ ማስያዝ የሚችል መሆኑን እንዲያውቁት የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት አዟል።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-08
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-07-08 12:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: ANRS Supreme Court
  • Published: Jun 07, 2026
  • Posted at: 2026-06-08T09:09:52.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders