የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በቅርስ ዙሪያ የሚገኙ የተለያዩ ዛፎችን ለመቁረጥ እና ባጃጅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለጐንደር ከተማ አስተዳደር ለባህልና ቱሪዝ መምሪያ እና ለገቢዎች መምሪያ አገልገሎት የሚውሉ የተለያዩ ግዥዎችን ማለትም፡-

  • በሎት 1 በቅርስ ዙሪያ የሚገኙ የተለያዩ ዛፎችን ለመቁረጥ
  • ቤሎት 2 ባጃጅ

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን፡- ማቅረብ የምትችሉ መረጃ

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ
  2. የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው (TIN)
  3. የገንዘብ መጠኑ ከ200,000 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርበታል
  4. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. የሚገዛውን ግዥ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ/ቢድ ቦንድ/ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ /በመክፈል ጎን/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 15 መውሰድ ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሃሳባቸውን አንድ ወጥ በሆኑ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ጎን ከ/አስ ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ተጫራቾች ዋጋውን በሚሞሉበት ወቅት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
  10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሙሉ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
  11. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በጎንደር ከ/አስ /ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ። ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ ጥሪአችንን አክበረው ባይገኙም ጨረታው በሌሉበት ይከፈታል። የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  12. ማንኛውም ተጫራች የሚቀርብ ቅሬታ ካለ ጨረታው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 የስራ ቀናት በኋላ የሚቀርብ ቅሬታ መ/ቤታችን የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን።
  13. ሁሉንም የሚገዙ እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ጎ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
  14. ለተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ ጎን/ከተ/አስ ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 126 0306 ደውሉ መጠየቅ ይችላሉ።
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Fax-058-111-7563 P.O box - 192 Tele- 058 126-0306

email- gontipco@ethionet.et 

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-24
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-24 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Gonder City Administration FEDB
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jun 09, 2026
  • Posted at: 2026-06-09T08:24:54.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders