የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን (Outsourcing cleaning services) ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፦ ECMA/NCB/18/2018

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለው በጀት የፅዳት አገልግሎት (Outsourcing cleaning services) ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፦

1 በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር በመክፈል ከባለስልጣኑ ፋይናንስና ግዥ ክፍል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

2 ተጫራቾች የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ፋይናንስና ከነካል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3 ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ክሊራንስ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረገጽ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን እንዲሁም የተፈረመና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4-ተጫራቾች ዋጋቸውን በመሙላት ባለስልጣኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ሰአት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

5-ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ15 ቀናት ብቻ ነው።

6- ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር ይገባዋል።

7-አሸናፊው ተጫራች አገልግሎቱ በተፈለገ ጊዜ አገልግሎቱን የመስጠት ሃላፊነት አለበት።

8- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበርያነት የብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

9-ተጫራቾች የቀረበውን ዝርዝር መስፈርት መሰረት በማድረግ የሚያቀርቡትን አገልግሎት ዝርዝር የቴክኒክ መግለጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

10-አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

11-ጨረታው ሰኔ 18 ቀን 2018 ከሰዓት በ8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከሰዓት በ8:30 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሸ ይከፈታል።

12-በጨረታው መክፈቻ ዕለት የተጫራቾች አለመኖር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም።

13-ባለስልጣኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14-ተጨማሪ ማብራርያ ካስፈለገ በአካል የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚጎ ገባ ብሎ ባለው ዋ/መ/ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባስስልጣን

የፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት

ምናዬ ኮርፖሬት ቢሮ ፓርክ፣ ክ/ከተማ ቂርቆስ፣ ወረዳ 9

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ስልክ 011-557-8327

ኢሜል: Procurement@ecma.gov.et

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-25
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-06-25 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን
  • Bid bond: 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር)
  • Bid document price: 300 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 10, 2026
  • Posted at: 2026-06-10T07:56:42.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders