የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የተለያዩ ማሽነሪዎች የኪራይ አገልግሎት ግዥ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ /አግ/13/09/2018
- የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የተለያዩ ማሽነሪዎች የኪራይ አገልግሎት ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/አግ/13/09/2018 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ኮርፖሬሽኑ ለሚፈጽመው የተለያዩ ማሽነሪዎች ኤክስካቫተር በጃክ ሃመር፣ ሎደር፣ ክሬን 50 ቶን ከሬን 30 ቶን፤ብትን ሲሚንቶ ማጓጓዣ ኮኮት፣ ሎው ቤድ ሃይ ቤድ 16 ሜ.ኪ የሚጭን ገልባጭ መኪና፣ ፎርክ ሊፍት ባለ 8 ቶን እና ባለ 5 ቶን የኪራይ አገልግሎት ግዥ ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነዳቸውን እና የዋጋ ሰነዳቸውን በአንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ መመሪያ ቁጥር 1070/2017 በፌዴራል መንግሥት ባለቤትነት የተያዙ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈጻጸም መመሪያ መሠረት ሲሆን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል።
- የተሟላ የአማርኛ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀረ በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 209 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 2ኛ ቢሮ ቁጥር 209 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ (unconditional) ቢድ ቦንድ ጋራንቲ ወይም ሲፒኦ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር ቢሮ 2ኛ ፎቅ ይከፈታል።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር፡- 011-185 53667 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-06-24
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-24 10:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Housing Corporation
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 300 ብር
- Published: Jun 10, 2026
- Posted at: 2026-06-10T08:31:59.000Z
- Buyer website: https://www.fhc.gov.et
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.