የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የተለያዩ ግዥዎችን መፈፀም ይፈልጋል
Description
የግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/ሴ/ህ/ማ/ጉ/ቢሮ (01/001-05/2019)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2010 በጀት አመት በ5 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ሎት ቁጥር |
የሚገዛው እቃ አገልግሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
|
ሎት 1 |
የተለያዩ የምግብ ግብዓት ግዥ
|
100,000.00 CPO |
|
ሎት2 |
የተዘጋጀ /የበሰለ/ የምግብ አቅርቦት ግዥ |
100,000.00 CPO |
|
ሎት3 |
የተለያዩ ጽዳት እቃዎች |
100,000.00 CPO |
|
ሎት4 |
የተለያዩ አልባሳት |
50,000,00 CPO |
|
ሎት5 |
የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ |
50,000,00 CPO |
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥና የፋይናንስ መመሪያዎች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ። ያላቸውና ማቅረብ
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ መዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 የብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአካውንት ቁጥር 100000650559 በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ከቢሮው ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በስፔስፊኬሽኑ መሰረት ብቻ ሞልተው እና አሽገው ኤንቨሎፕ ላይ ኦርጂናልና ኮፒ ብለው በመለየት የግዥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
7. ተጫራቾች ሌሎች መረጃዎችን፣ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆን እናሳውቃለን።
8. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው፤ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
9. ተጫራቾች ናሙና ለተጠየቀባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው
10. የጨረታ ማስከበሪያ በ CPO ነው
ማሳሰቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን 4፡0 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
አድራሻ፣ አ/አ/ሴ/ህ/ማ/ጉ/ቢሮ ዳጃች ውቤ ከጊዮርጊስ ቤተክሪስቲያን ወደ አፍንጮ በር በሚወስደው መንገድ የስድስት ኪሎ ፈረንሳይ ታክሲ መጫኛ ጋር ህንጻ 1888 ላይ 2ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 09 42 12 97 92/ 09 47 95 17 60/ 109 27 21 27 65
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-06-23
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-23 10:30
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Administration Women, Youth and Social Affairs
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published: Jun 11, 2026
- Posted at: 2026-06-11T08:28:01.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.