የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለኤክስፖርት እና ለአገር ውስጥ ግብይት ምርቶች መያዣነት የሚውሉ የተለያዩ መጠን ያላቸው የፕላስቲክ ከረጢቶች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር፦ኢ.ን.ሥ.ኮ ማዕከል ግዥ /ብግጨ 08/2018
የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለኤክስፖርት እና ለአገር ውስጥ ግብይት ምርቶች መያዣነት የሚውሉ የተለያዩ መጠን ያላቸው የፕላስቲክ ከረጢቶች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የመንግስት የግዥ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይጋብዛል።
የግዥው ዓይነት፡- የተስያዩ መጠን ያላቸውን ፕላስቲክ ከረጢት ዓይነቶች፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ወቅታዊ የግብር ድጋፍ ደብዳቤ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ እና የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ እነዚህ ሰነዶች በቴክኒክ ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ መካተት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ/ በመክፈል ሰኔ 15 ቀን 2018ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30- 6፡30 እና ከሰዓት 7፡30-11:30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 –6፡30 ማመልከቻ በመያዝ በኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ብሎክ 2፣ 1ኛ ፎቅ ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በኮርፖሬሽኑ ስም ሆኖ መቅረብ አለበት፡፡ ኢንሹራንስ ቦንድ ወይም ቼክ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች የቴክኒክ እና የፋይናንስ ሰነዶችን ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በዋናው መ/ቤት የመሰብሰቢያአዳራሽ ይከፈታል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ የፕላስቲክ ከረጢት ዓይነቶች ናሙና (Sample) ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ/ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በማቅረብ ውል ይፈጽማል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ደብረዘይት መንገድ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርጫፍ ፊትለፊት
ፖ.ሳ.ቁ.7858
ስልክ ቁጥር 011 4167345/011 4669336
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-07-01
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-07-01 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Trade Works Corporation
- Buyer address: ደብረዘይት በሚወስደው መንገድ በቅሎ ቤት ከዳሸን ባንክ ዋናው መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት
- Bid bond: 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/
- Bid document price: 1,000.00 ብር
- Published: Jun 12, 2026
- Posted at: 2026-06-12T08:24:19.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.