Cables, conduits and accessories

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አገልግሎት ላይ የሚዉል የተለያዩ የኤሌትሪክ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ/ NCB/

ጨረታ ቁጥር-SIPDC-YIAIP/NCB/-05/18

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኮርፖሬሽን ለይ /ዓለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ አገልግሎት የሚዉል የተለያዩ የኤሌትሪክ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሕጋዊ ቅድመ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ፣የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በአየር ላይ ይቆያል።
  4. የጨረታ ሠነዱ በኮርፖሬሽኑ የኮፓሬት ሰርቪስ ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ16ኛዉ ቀን በ6፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል። 16ኛዉ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታዉ በቀጣይ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል። ዘግይተዉ የሚመጡ ሠነዶች ተቀባይነት አይኖራቸዉም።
  5. ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግሥት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው ውል ባለመፈጸም የታገዱ መሆን የለባቸዉም።
  6. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ በኮርፖሬሽኑ በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን መውሰድይችላሉ።
  7. ተጫራቾች በዓይነትም ሆነ በመጠን በጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል መሣተፍ ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO/BlD Bond ለ90 ቀን በኮርፖሬሽኑ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  9. የዉል ስምምነት የማይተገበር ተጫራች ያስያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይሆናል።
  10.  በጨረታው ለመሳተፍ ወይምለመወዳደር የሚወጡ ወጪዎች ቢኖሩ ኮርፖሬሽኑ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  11. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ተንተርሶ ሌላ ዋጋ መስጠት ክልክል ነው።
  12. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃዎቻቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ አማርኛ መሆን ይኖርበታል።
  13. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ገጽ ላይ፣ስም፣ፊርማ፣ማህተም፣ሙሉ አድራሻቸውን ማኖር አለባቸው።
  14.  ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ለሚኖራቸው ጥያቄ እና ማብራሪያ የጨረታ ጊዜው ከመጠናቀቁ /10/ አስር ቀን በፊት ከታች በተገለጹት ስልክ ቁጥሮች እና አድራሻ በመደወልና በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።ሆኖም ጥያቄው ወይም ማብራሪያው በጽሁፍ የተደገፈ መሆን አለበት።
  15.  ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን፡- 0994165729/0462125978 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አድራሻ: ፒያሳ በሚገኘው አዋሻ ባንክ አ.ማ ሕንፃ 6ኛ (ስድስተኛ) ፎቅ ቢሮ ቁጥር

R5- ሀዋሳ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት  ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-27
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን በ6፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-27 14:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን በ8፡00 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Sidama Industrial Parks Development Corporation
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jun 12, 2026)
  • Posted at: 2026-06-12T08:32:04.000Z
← Back to all tenders