ናሽናል ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር charcoal (የምግብ ማብሰያ ከሰል) ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማጫረት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ናሽናል ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር charcoal (የምግብ ማብሰያ ከሰል) የሚፈለገው በወር 2,500.00 ቶን (2,500,000 ኪ.ግ) ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማጫረት ይፈልጋል::

በመሆኑም ተጫራቾች፡-

  • በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃቸውን ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ::
  • ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 3 ወራት ህጋዊ ሆኖ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) ብር ወይም የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው::
  • ተጫራቾች ከላይ የተገለጸውን charcoal (የምግብ ማብሰያ ከሰል) የአንድ ቶን (የአንድ ኪ.ግ) ዋጋ ከቫት በፊት በመሙላት በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 20 የስራ ቀናት አዲስ አበባ ጦር ሀይሎች አዋሽ ወይን አካባቢ ኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ ህንጻ ስልክ፡ 251-114-421928/0934-64-64- 77/0960-36-71-36 ግዢ ክፍል እና ድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ ኢማ ስልክ ቁጥር 0930- 28-34-90/0935-98-50-83 ግዢ ክፍል በታሸገ ፖስታ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ::
  • ጨረታው ሰኔ 29/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ ሐምሌ 3/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ በሚገኘው ናሽናል ሲሚንቶ ኢማ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
  •  ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::

ማሳሰቢያ፡-

  • ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይሰጥበታል:: መ/ቤቱም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው::

ናሽናል ሲሚንቶ አ/ማ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-06
  • Publishing entity: National Cement S.C.
  • Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • Published: Jun 14, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders