ፀደይ ባንክ አ.ማ. የሴራሚክ ማምረቻ ፋብሪካ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የኃራጅ  ሽያጭ ማስታወቂያ

ፀደይ ባንክ አ.ማ. ለአቶ እንግዳየሁ ፋንታሁን ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዘዉን በአብክመ እንጅባራ ከተማ ቀበሌ የካርታ ቁጥር 77/2010 በአቶ አክሊሉ መኮነን ስም ተመዝግቦ የሚገኘዉን 10,000 ካ ሜ ስፋት ያለዉ የሴራሚክ ማምረቻ ፋብሪካ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ጫረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም ተጫራቾች ለጫረታ ከመቅረባቸዉ በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ መጫረት እንዲችሉ ይጋብዛል፡-

1. የቤቱ የጫረታ መነሻ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር ግምቱ 51,094,692.5 (ሃምሳ አንድ ሚሊዮን ዘጠና አራት ሺህ ስደስት መቶ ዘጠና ሁለት ብር ከሃምሳ ሳንቲም) ብቻ

2. ተጫራቾች የቤቱን ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 1/4 (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ) በጸደይ ባንክ አማ ስም በማሰራት ለጫረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3. የጫረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠዉ የጫረታዉ ዉጤት በሚመለከተዉ አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠዉ ብቻ ይሆናል።

4. በጫረታዉ የሚሳተፈዉ በህግ ሰዉነት ያገኘ ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደምብ፤ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ዉክልና ማቅረብ አለበት።

5. የጫረታዉ አሽናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ዉስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጫረታ ያሸነፈዉን ንብረት መረከብ ይኖርበታል:: አሸናፊዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጨራታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ - ለባንኩ ገቢ ይሆናል።

6. በጫረታዉ ለተሸነፉ ተጫራጮች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።

7. የጫረታ አሸናፊዉ ከሚገዛዉ ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ ጋር የተያያዙ ማናቸዉም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝዉዉሩ ጋር የሚገናኙ ማንኛዉንም ወጭዎች ገዢ ይሸፍናል/ ይከፍላል::  ዉዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ  ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረዉና የክፍያ ጊዜዉ ላልደረሰ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር እንዲዋዋል ይደረጋል።

8. ተጫራቾች ቤቱን /ድርጅቱን/ በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።

9. ጫረታዉ የሚካሄደዉ ሀምሌ 3/2018 ከጠዋቱ 3.00---5.00 የተጫራቾች ምዝገባ፤ ከ5.00 እስከ ቀኑ 6.00 ሰዓት ጫረታ በእንጅባራ ከተማ፤ ፀደይ ባንክ እንጅባራ ዲስትሪክት ቢሮ

10. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጫረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

 ለተጨማሪ መረጃ፡- ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት
በስ.ቁ +251918779825 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።


Tender details

  • Deadline: 2026-07-10
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid opening: 2026-07-10 11:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
  • Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jun 14, 2026
  • Posted at: 2026-06-15T12:41:01.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders