የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት የተለያዩ እቃዎችን/ አገልግሎቶችን ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ለሁለተኛ እና ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት፡-

ለሁለተኛ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የእቃ የአገልግሎት ግዥ

ሎት 1 የፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒ፤ ፋክስ ስካነር ጥገና እና ቀለም ሙሌት ግዥ

ለሦስተኛ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የእቃ/ የአገልግሎት ግዥ

ሎት 2 የፓወር ኢንቨንተር Power inventor ጥገና አገልግሎት

ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው።

1. ተጫራቾች በዘርፋ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደስ የ2018 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተኬት ያላቸው፣ የገቢዎች ክሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. ተጫራቾች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት የታደሰ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

4. በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ፌዴራል ፖሊስ የግል የተቋማት ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የታደሰ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ CPO ብቻ ማስያዝ አለባቸው።

6. ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መግለፅና መሆን አለበት። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻውን፣ ፊርማውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።

8. ጨረታ ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፡፡ ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት። ስለዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት።

9. ጨረታ በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል።

10. ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር ወይም በመቀነስ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል።

11. ተጫራቾች የሚመረቱትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም የታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል።

12. ተጫራቾች በሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ Bid document መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል። የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ / CPO/ ለብቻው እና ፋይናሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባ አለባቸው።

13. የጨረታ ሂደት የቴክኒክ ግምገማ ለሎት 1 ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ከቴክኒክ ሠነድ ግምገማና ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ ውጤት (60%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምግማ ውጤት (40%) ሲሆን እንደዚሁም ለሎት 2 ድርጅቱ በሚያወጣው ስፔስፊኬሽን/Specification/ ግምገማ (40%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምግማ ውጤት (60%) ድምር ውጤት አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ። ነገር ግን ቴክኒካልና ስፔስፊኬሽን/Specification/ ግምገማ ሰነድ ወይም ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሺያል ሠነድ እንደማይከፈት እንዲታወቅ። የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 011 553 0767 / 011 515 7337

የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-25
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-25 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Filwuha Service Enterprise
  • Bid bond: 25,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
  • Published: Jun 16, 2026
  • Posted at: 2026-06-16T08:48:22.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders