የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ 2018 በጀት ዓመት የፅዳት ዕቃ እና የሴቶች የግል ንፅህና መጠበቂያ፣ ፍራሽ፣ አንሶላ፣ ትራስ እና ትራስ ጨርቅ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ 2018 በጀት ዓመት ለክልሉ ጤና ቢሮ እና ለተጠሪ ተቋማት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን በመጋበዝ እንደሚከተለው በሎት በመከፋፈል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የፅዳት ዕቃ እና የሴቶች የግል ንፅህና መጠበቂያ
  • ሎት 2 ፍራሽ አንሶላ ትራስ እና ትራስ ጨርቅ

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

  • በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
  • የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል
  • የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል
  • የግብር ከፋይ መለያ ምስክር ወረቀት /TIN Number/ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ NAT| ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል መሆን ይኖርባቸዋል በመሆኑም ተጫራቾች ሰነድ በእያንዳንዱ ሎት መግዣ የማይመለስ ብር 1,500 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ቀርበው በመክፈል ዘወትር በመንግስት ሥራ ሰዓት 15 /አስራ አምስት ቀናት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ግዥ ክፍያ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት በማቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  • ሎት 1 የፅዳት ዕቃ እና የሴቶች የግል ንፅህን መጠበቂያ 100,000/ አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ
  • ሎት 2 የፍራሽ አንሶላ ትራስ እና ትራስ ጨርቅ 100,000 ብር/ አንድ መቶ ሺህ ብር/ብቻ
  • በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ስም CPO/የባንክ ጋራንት/ በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመጻፍ በሰመ/በሙጫ በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/የመንግስት የሥራ ቀናት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ግዥ ክፍያ ንብ/ አስ/ር ዳይሬክቶሬት በማቅረብ ለዚህ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ 1 አንድ /ኦሪጂናል እና 2/ሁለት/ ኮፒ ፖስታዎች ለየብቻቸው በሰም /በሙጫ/ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን አድራሻ፣ ማሕተምና ፊርማቸውን በግልጽ መሙላት ይኖርባቸዋል።
  • የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከቀኑ 5፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። በመክፈቻው ዕለት የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።
  • አሸናፊው ድርጅት በተወዳደረበት ቦታ ንብረቱን የማቅረብ ግዴታ አለበት።
  • ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መ/ቤቱ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር- +251 4734508

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-06
  • Publishing entity: South West Ethiopia People Regional State Health Bureau
  • Bid bond: 100,000.00 ብር በየሎቱ
  • Bid document price: 1500.00 ብር በየሎቱ
  • Published: Jun 18, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders