ጣምራ ለማበራዊ ልማት ድርጅት በአዲስ አበባ ፣ በኦሮሚያ ክልል እየተገበረ ለሚገኘው ፕሮጀክቶች የሚውል መልሶ ጥቅም ላይ የሚውል የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ውጤቶች ላይ የስፌት ስልጠና የሚሰጡ፣ እዲሁም ለስልጠና የሚያስፈልጉትን የስፌት ማሽን እና ሌሎች ቁሳቁሶችን የሚያቀርቡ ድርጅቶች በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል

★ Featured

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ጣምራ ለማህበራዊ ልማት ድርጅት ከተመሠረተበት 1990 ዓ.ም ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 28 ዓመታት በወጣቶች ልማት፣ በሥነ-ተዋልዶ ጤና፣ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሰውን ጾታዊ ጥቃት በመከላከል፣ በአካባቢ ጥበቃና የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭትና በሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ዙሪያ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ክልሎችና በአዲስ አበባ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ለዚህም ተግባሩ ድርጅታችን ላበረከተው የማኅበረሰብ አቀፍ ጉልህ አስተዋኦ ከሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር፣ ከኦሮምያ ክልልና ከኢፊዲሪ መንግስት የሠርትፍኬት፣ የዋንጫ፣ የቦታና የመኪና ሽልማቶችን ያገኘ አንጋፋ ድርጅት ነው፡፡

ድርጅታችን ጣምራ ለማበራዊ ልማት ድርጅት በአዲስ አበባ ፣ በኦሮሚያ ክልል እየተገበረ ለሚገኘው ፕሮጀክቶች የሚውል መልሶ ጥቅም ላይ የሚውል የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ውጤቶች ላይ የስፌት ስልጠና የሚሰጡልንን፣ እዲሁም ለስልጠና የሚያስፈልጉትን የስፌት ማሽን እና ሌሎች ቁሳቁሶችን የሚያቀርቡልንን ድርጅቶች ለማወዳደር ጨረታ ያወጣን ሲሆን ዝርዝር የጨረታ ሃሳቡን እና የሚፈለገውን የስፌት ማሽን ዝርዝር የያዘውን ዶክመንት የማይመለስ 200 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ በመግዛት ጨረታውን መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን ተጫራች ድርጅቶች ተወካይ መላክ የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

አድራሻ - ከጃክሮስ ወደ ሳህሊተ ምህረት ቤተክርቲያን በሚወስደው መንገድ አቢሲኒያ ባንክ ጀርባ እንገኛለን

ለበለጠ መረጃ - 0982024874 ይደውሉ፡፡

Deadline – June 24/ 2026


Tender details

  • Deadline: 2026-06-24
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-06-24 12:00
  • Bid opening (note): No Specific Date and Time
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Tamra Economic Development Organization
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Jun 18, 2026
  • Posted at: 2026-06-18T09:30:58.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders