አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ. የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ስርዓት ለማቅረብ የተቋቋመ እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የስራ ፈቃድ የተሰጠው የፋይናንስ ተቋም ሲሆን ለመጋዘን ህንጻ የጥበቃ አገልግሎት ሲሆን ለጥበቃው አገልግሎት አስፈላጊ ግብዓቶችን በሙሉ ተጫራቹ ችሎ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር የመጋዘን ጥበቃ-02/2018

አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ ኤማ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 እና በማሻሻያ አዋጅ 807/2005 መሰረት የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ስርዓት ለማቅረብ የተቋቋመ እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የስራ ፈቃድ የተሰጠው የፋይናንስ ተቋም ሲሆን ለመጋዘን ህንጻ የጥበቃ አገልግሎት ሲሆን ለጥበቃው አገልግሎት አስፈላጊ ግብዓቶችን በሙሉ ተጫራቹ ችሎ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ጋብዘናል።

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጣቸው የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ወቅታዊ የሆነ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወይም ከሚመለከተው የመንግስት አካል የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ እና ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።

3. ተጫራቾች በዘርፉ አምስት አመትና ከዚያ በላይ የስራ ልምድ ያለውና የድርጅታቸውን አጠቃላይ ሁኔታ መግለጫ(company profile) ማቅረብ የሚችሉ፣ የሚያቀርቧቸው የጥበቃ ባለሙያዎች የትምህርት ዝግጅት 8ኛ ክፍልና ከዚያ በላይ ያጠናቀቁ፣ የጥበቃ አገልግሎት ሙያ ወይም ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ ሆኖ በጥሩ ስነምግባር የታነጹ እና ቢያንስ በሙያው 2 አመትና ከዚያ በላይ የጥበቃ አገልግሎት ልምድ ያላቸው ሰራተኞችን ማቅረብ የሚችል።

4. ተጫራቾች ለተሰማሩበት ድርጅት ለሚፈጠር አደጋ ሙሉ ኢንሹራንስ የገቡ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

5. ተጫራቾች ከዚህ በፊት ሲሰሩ ከቆዩበት ድርጅቶች ቢያንስ ከ3 መ/ቤት የመልካም ስራ አፈጻጸም ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ሰነድ ለየብቻው በማሸግ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት የጨረታ ማስከበሪያውን ከኦርጅናል ቴክኒካል ፖስታው ውስጥ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።

8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 24/2018 ዓ.ም የማይመለስ 500(አምስት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ መታሰቢያ ህንጻ ጎን በሚገኘው አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ ኢማ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ፣ ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

9. ተጫራቾች የጨረታ ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ እስከ ሰኔ 24/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. ጨረታው በቀን 24/10/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ 4ኛ ፎቅ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል።

11. ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተከርስትያን ወደ 6 ኪሎ መሄጃ ድንበሬ መታሰቢያ ህንጻ ጎን

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09 33 00 73 89 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-01
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-07-01 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Capital Goods Finance Business S.C
  • Buyer address: Arat Kilo next to Tourist hotel Ethiopian Post service organization building 3rd floor, procurement administration directorate office
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Jun 19, 2026
  • Posted at: 2026-06-19T08:12:11.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders