የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጄንሲ ለዋናው መ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የቢሮ ጽዳት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ዓመታዊ ውል በመያዝ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር አ.ገ/መ/ኮ/ኤ/01/2019 ዓ.ም

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጄንሲ ለዋናው መ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የቢሮ ጽዳት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ዓመታዊ ውል በመያዝ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው

3.የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያላቸው!

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣

5. የቢሮ የጽዳት አገልግሎት _ ዝርዝር _ መገለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በአብክመ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ13/10/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 28/10/2018 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በተቋሙ ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ወይም አማራ ባንክ 9900020983896 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኦርጅናል ከፋይናንሻል ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስያዝ አለባቸው።

8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማለትም ዋና እና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በተለያየ ፖስታ በአንድ ኢንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት /በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ13/10/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ቀን 28/10/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤

9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት አዳራሽ ወይም ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 03 በቀን በ28/10/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 8፡30 ይከፈታል፣

10. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

11. ኤጀንሲዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 222 1100 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 322 05155 / 058 222 1107 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

13. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና ማህተም ማድረግ አለባቸው። በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።

ባህር ዳር ፖ.ሣ.ቁ.382

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጄንሲ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-05
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-07-05 14:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara National Regional State Rural Road Construction Agency
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Jun 20, 2026
  • Posted at: 2026-06-20T07:55:21.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders